Skip to main content

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ2018 ዓ.ም 

ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም አስጀመሩ 

ሆሳዕና፣ሰኔ 17/2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በከምባታ ዞን 

ዱራሜ ከተማ በዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ ሆስፒታል 

ግቢ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አስጀምረዋል። 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ ከ530 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለተከላ 

መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። 

እስከ ሐምሌ 25 ፣ 2018 ባሉት ቀናት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች 

የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል። 

የአረንጓዴ አሻራ ሀገርን ከሚለውጡ ፕሮግራሞች መካከል አንዱ ነው 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ 

ችግሮችን ለመቅረፍ የላቀ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል። 

የአረንጓዴ አሻራ ለምግብነት፣ለመድሀኒትነት፣ለቁሳቁስ መስሪያነት እና 

ለሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን 

ተናግረዋል። 

በተለያዩ ጊዜያት እየተተከሉ ያሉ ችግኞች የጽድቀት መጠን እየጨመረ 

ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

የክልሉ ህዝብ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ በንቃት እየተሳተፈ ነው 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም የከርሰ ምድር እና የገጸ ምድር የውሃ 

አካላት መጨመር ስለመስተዋሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል። 

የክልሉ ህዝብ እስከ ሐምሌ 30/2018 በዘመቻ ለሚካሔደው የአረንጓዴ 

አሻራ ፕሮግራም ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል። 

በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ የክልል፣የዞን እና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች 

ተሳትፈዋል።

Image