Skip to main content

በክልሉ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በተሰራው ስራ 

ካለፉት ዓመታት የተሻለ ለውጥ ይጠበቃል - ርዕሰ 

መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 1/2018 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 3ኛውን ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር 

አቀፍ ፈተና በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት የፈተና አሰጣጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 

ከዚህ ቀደም ከምናውቀው የምዘና ዘዴዎች ወደ ዲጅታል በመለወጥ ላይ 

ይገኛል።

በክልላችንም በ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሚወስዱ 

ከአጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 61 በመቶው በበይነ-መረብ እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

ይሄም በክልል ባለፉት ዓመታት ከነበረው በበይነ መረብ ፈተና የመስጠት አቅም

በእጅጉ ያደገ ነው ብለዋል።

በሚቀጥለው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆችን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች 

በቂ ዝጅግት ተደርጎ ቁጥሩ ለማሳደግ ይሰራል ነው ያሉት።

በክልሉ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት ልዩ ልዩ ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹት 

ርዕሰ መስተዳድሩ የተማሪዎች የክፍል ውስጥ ምዘና ውጤት ከመከታተል ጀምሮ 

የውጤት ማሻሻያ ስልቶችን በመቅረጽ ተግባራዊ ስለመደረጉ ገልጸዋል።

በተለይም በክልሉ በተከታታይ ዓመት አንድም ተማሪ ማሳለፍ ካልቻሉ ትምህርት 

ቤቶች የማለፍ ተስፋ ያላቸው 886 ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ገብተው ልዩ የማጠናከሪያ 

ትምህርት እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

የእነዚህ ስራዎች ድምር ውጤት በተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር ላይ ለውጥ 

ያመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል።

Image