“በጎነት ከውስጥ መልካምነት የሚመነጭና ሀገርን ወደ ላቀ ከፍታ
የሚያሻግርታላቅ አገልግሎት ነው”፦ ርዕሠ መስተዳድር
እንዳሻውጣሰው(ዶ/ር)
ሆሳዕና፣ሐምሌ 3/2018 ፦"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ
የሚንቀሳቀሰውሀገር አቀፍ የወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት
ቡድንበሆሳዕና ከተማ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
በዕለቱ በተዘጋጀው የአቀባበል መረሐ ግብር ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ
ክልልርዕሠ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለበጎ ፈቃደኞቹ የእንኳን
ደህናመጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
“በጎነት ከውስጥ መልካምነት የሚመነጭና ሀገርን ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሻግር
ታላቅአገልግሎት ነው ሲሉ ርዕሠ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ተናግረዋል።
በጎፈቃደኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ 'ፒስ ኮር' (Peace Corps) እና የ'ስካውት'
ንቅናቄዎችያሉየረጅም ጊዜ ታሪካዊ መሠረቶች ያሉት መሆኑን አስታውሰዋል።
ይህ መልካምእሴት በአሁኑ ወቅት ከለውጡ በኋላ በተከታታይና በተጠናከረ
መልኩእየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ይህመርሃ ግብር የወደፊቷን ኢትዮጵያ የሚረከቡ ወጣቶች ማህበረሰባቸውንና
ሀገራቸውንበቅርበት እንዲረዱ፣ እርስ በእርስ የዕውቀትና የባህል ልውውጥ
እንዲያደርጉምቹዕድል የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል።
በሌሎች ሀገራት ሰዎች እስከ 70 እና 80 ዓመታቸው ድረስ በጉልበት ሀገራቸውን
እንደሚያገለግሉበመጥቀስ፣ የሀገራችንም ወጣቶች የአገልግሎት ዘመናቸውን
ማራዘምእንዲችሉ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።
አያይዘውም ከሀምሌ 28 ቀን ጀምሮ የሚካሄደውን ታሪካዊ ሀገራዊ ምክክር
ወጣቶችበሀሳብና በሁሉም ረገድ እንዲደግፉ በጥብቅ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያውያን መክረውና ተስማምተው እንዲወጡ የበጎ ፈቃድ ቡድኑ አባላት
የበኩላቸውንአዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።
ርዕሠ መስተዳድሩ በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ በጎ ፈቃደኞቹ የመጡበትን
መልካምየልማትና የአገልግሎት ዓላማ በተሳካ ሁኔታ እንዲወጡና ቆይታቸው
የሰላምናፍሬያማ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።