በክልሉ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ 1 ነጥብ 87 ቢልዮን ሀብት መሰብሰብ
ተችሏል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
ሆሳዕና፣ነሐሴ 1/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ
ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )ለምክርቤቱ
ትላንት ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት በክልሉ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ 1 ነጥብ
87 ቢልዮን ሀብት መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።
በዚህም አዲስ የቅድመ-አንደኛ 72 አንደኛና መካከለኛ 30፣ ሁለተኛ ደረጃ 5 ትምህርት
ቤቶች መገንባታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አብራርተዋል።
በሁሉም እርከን የአዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣የነባር ክፍሎች ጥገና፣ ሌሎች
የትምህርት ግብአቶችን ለማሟላት ጥረት መደረጉን አስረድተዋል።
በክልሉ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያጋጠመውን ስብራት መጠገን የሚያስችሉ ዕቅዶች
ተዘጋጅተው በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በዘርፉ በተደረገ ሁሉን አቀፍ ጥረት የተማሪዎች ሥነ-ምግባርና ውጤት እንዲሁም
በትምህርት ጥራት ላይ መሻሻል ታይቷል ብለዋል፡፡
በክረምት ወቅት የተማሪዎችን ውጤትን ለማሻሻል በመምህራንና በበጎ ፈቃደኛ
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አማካይነት ለ294 ሺ 284 ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት
ተስጥቷል፡፡
በበጀት ዓመቱ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ህብረተሰቡ በገንዘብ፣ በአይነት፣ በጉልበት
እና በዕውቀት የላቀ ተሳትፎ ስለማድረጉም ጠቁመዋል።