በክልሉ በገቢ እና በንግድ ስርዓቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት
አስገዳጅ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል:-
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር
ሆሳዕና፣ነሐሴ 4/2018፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ እና
የክልሉ የንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ የህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር፣ ኑሮ
ማረጋጋት እና የታክስ ህግ ተገዢነት ለማረጋገጥ የተዘጋጀ የምክክር
መድረክ እየተካሄደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
በምክክር መድረኩ እንደገለጹት በክልሉ በገቢ እና በንግድ ስርዓቱ ላይ
መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት አስገዳጅ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ትኩረት
ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በክልሉ በገቢ እና በንግድና ገበያ ልማት ሴክተሮች ወቅታዊ አጀንዳ ላይ
በመወያየት ለቀጣይ ስራ ተግባቦት መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የልማት ስራዎቻችንን ስኬታማ ለማድረግ የመወያየት እና የመመካከር
ባህል እያደገ መጥቷል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል።
የታክስ ህግን ማስከበር እና ገቢን ማሳደግ ላይ የጋራ ጥረት ይጠይቃል ያሉት
ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱ
በሶስት መቶ በመቶ አድጓል ብለዋል።ነገር ግን የክልሉ ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው
ገቢ አንጻር አሁንም ቀሪ ስራ እንዳለ አመላክተዋል።
በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በአመት በአማካይ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱን ከ15
እስከ 20 ቢሊየን በማሳደግ የክልሉን ገቢ የማመንጨት አቅም ከ120 ቢሊየን ብር
በላይ ከፍ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
በአምስት ዓመታት ውስጥ በዘርፉ ጠንክረን የምንሰራ ከሆነ የክልሉን ገቢ በ200
ቢሊየን ብር ማሳደግ እንደሚቻልም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የገቢ አሰባሰብ ስርዓት እያደገ ሲሄድ የክልሉን ከተሞች የመሰረተ ልማት ፍላጎት
ማሟላት እንደሚያስችልም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
የክልሉን ከተሞች በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ማሳደግ የሚያስችል አዲስ
እቅድ ማዘጋጀት ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በክልሉ በየአመቱ ከ10 እስከ 15 ቢሊየን ብር ከደረሰኝ ገቢ ብቻ መሰብሰብ
እንደሚቻል ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
በየጊዜው እያደገ ለመጣው የህዝብ የልማት ፍላጎት ምላሽ መስጠት የሚቻለው
ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ሲቻል ብቻ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው
ጠቅሰዋል።
በክልሉ የንግድ ስርዓቱን መቆጣጠር እና መስመር ማስያዝ ይገባል ያሉት ርዕሰ
መስተዳድሩ በሀገሪቱ የሚወጡ ደንቦች እና መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ
አስፈላጊ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
በንግድ እና በገቢ ሴክተሮች እያጋጠመ ያለውን ችግር በመፍታት ረገድ የላቀ
ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እያጋጠመ ያለውን የዋጋ ንረት መቆጣጠር ተገቢ ነው
ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ
በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
በክልሉ ያሉትን ጸጋዎች በማልማት ምርታማነትን ማሳደግ የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር
ረገድ ጉልህ አበርክቶ እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በክልሉ አስገዳጅ የሆ የህግ ማስከበር ስራ ላይ በልዩ ትኩረት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል
ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ጥቂቶች ብቻ የሚዘውሩት የንግድና የገቢ ስርዓት ሊኖር
አይገባም ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።