admin11
Fri, 09/04/2026 - 10:31
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) ከቻይናዉ ሁዋዬ
ማዕድን ማዉጣትና ፕሮሴሲንግ ካምፓኒ ጋር በጋራ መስራት
በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር አደረጉ
ሆሳዕና ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) ከቻይናዉ ሁዋዬ ማዕድን
ማዉጣትና ፕሮሴሲንግ ካምፓኒ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ
ሁኔታዎች ላይ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸዉ ምክክር አድርገዋል።
ካምፓኒዉ በተለይም በሴራሚክስ ማምረት ስራ ያካበተዉን ልምድ
መነሻ በማድረግ በክልሉ ለሴራሚክስ ኢንዳስትሪ በሚሆኑ ግበዓቶች
ዙሪያ የካምፓኒው ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ሊ ሺሚንግ ከክቡር
ርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በዝርዝር ተወያይተዋል።
ካምፓኒዉ በክልሉ የዉጭ ቀጥተኛ ኢንቬስትመንትን ለማበረታታትና
ለመሳብ በተቋቋመዉ የላይዘን መስሪያ ቤት አማካኝነት ቀደም ሲል
በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ የመስክ ምልከታ በማድረግ
ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸዉን ማረጋገጡ ተመልክቷል።
Image