Skip to main content

ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) የስራ ርክክብ አደረጉ 

ሆሳዕና፣መስከረም 27/2019፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ 

መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ከቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው( ዶ/ር ) ጋር የስራ ርክክብ አደረጉ 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) 

ከቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ጋር በጽ/ቤታቸው 

የስራ ርክክብ አድርገዋል። 

የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት 

ባለፉት ሶስት ዓመታት ክልሉ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ በማለፍ ውጤታማ 

ስራ ማከናወን መቻሉን አብራርተዋል። 

ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ፕሮጀክቶች 

ተግባራዊ መደረጉን በአብነት ጠቅሰዋል።

ባለፉት ሶስት ዓመታት ሰርተን ያሳካናቸው ፣ ጀምረን ያላጠናቀቅናቸው ጉዳዮች 

እንዲሁም በረጅም ጊዜ አቅደን የጀመርናቸው ስራዎች አሉ ሲሉም ዶ/ር እንዳሻው 

ጠቁመዋል። 

በቅብብሎሽ ሂደት ውስጥ ስራን ጀምሮ ማጠናቀቅ ተገቢ ነው ያሉት ዶ/ር እንዳሻው 

የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉንም አካላት ቁርጠኝነት ይጠይቃል 

ብለዋል። 

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ከምስረታ እስከ አሁን የነበረው ጉዞ፣የክልሉ መንግስት 

የ2019 በጀት አመት እቅድ እንዲሁም የክልሉን መንግስት የሰባት ዓመታት መሪ 

እቅድ ለአዲሱ ርዕሰ መስተዳድር አስረክበዋል።

ለአዲሱ ርዕሰ መስተዳድር መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል። 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በበኩላቸው 

በሀገሪቱ ከውስጥም ሆነ ከውጭ እያጋጠመ ያለውን የጠላት ሴራ በማክሸፍ የመደመር 

መንግስት እውን መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

አዲስ ክልል መስርት፣ተቋም አደራጅቶ፣የሰው ሀይል በማሰማራት፣የክልሉን 

ህዝብ አንድነት ጠብቆ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እድለኝነት ነው ሲሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

የክልሉ መንግስት አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ማብቃት የቻለ ክልል 

መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል። 

ስልጣን የግል ጥቅም መገልገያ ሳይሆን ህዝብ የምናገለግልበት፣ሀገር የምንገነባበት 

ትልቅ ኃላፊነት ስለመሆኑም አስረድተዋል።

ህዝብ የሰጠንን አደራ በቁርጠኝነት ለመወጣት ጥረት እናደርጋለን ሲሉም 

አስረድተዋል።

Image