ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን
ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በኢንሴኖ ከተማ
የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው
ሆሳዕና፣ግንቦት 14/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን
ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በምስራቅ ጉራጌ ዞን
በኢንሴኖ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ
የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው
በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣
የክልል፣የዞን የስራ ኃላፊዎች እና የብልጽግና ፓርቲ
ደጋፊ አባላት ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ
በሚገኘው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ምርጫዬ ብልጽግና ነው፣
የምግብ ሉአላዊነት ተምሳሌት፣በዲጂታል ኢትዮጵያ ነገን መገንባት፣
ጸጋን ወደ ሀብት፣ብልጽግናን እመርጣለሁ አሻራዬን አኖራለሁ፣
ትላንትን ማከም ነገን መተለም እና ሌሎችም መፈክሮች
ተስተጋብተዋል።
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን
ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በኢንሴኖ ከተማ
የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው