በልዩ ትኩረት እየተመሩ የሚገኙ ተግባራት አፈጻጸም እየተሻሻለ መጥቷል፤
የአፈጻጸም ልዩነቶች ግን አሁንም ማነቆ ሆነዋል
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፤
ሆሳዕና ፣ሰኔ 3 ፣ 2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ በልዩ ትኩረት እየተመሩ የሚገኙ ተግባራትን
ወቅታዊ የአፈጻጸም ሁኔታ በበይነ መረብ አማካይነት ዛሬ ገምግመዋል።
በመድረኩ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬን ጨምሮ፣ የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣
የሚመለከታቸው የክልሉ ካብኔ አባላት፣ የዞኖቾ እና ልዩ ወረዳዎች
ዋና አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል ።
የአፈጻጸም ግምገማው በፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ፣
በመሶብ _የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ዝግጅት፣
በኢትዮ _ኮደርስ ስልጠና፣ በገቢ አሰባሰብ ፣በከተማና በገጠር ኮሪደር ልማት፣
በሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች አፈጻጸም፣የኑሮ ውድነትትን ከማረጋጋትና
የነዳጅ አቅርቦትንና ስርጭትን በተመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ መሆኑ ተመልክቷል ።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ በመድረኩ ማጠቃለያ እንደገለፁት ፣
በልዩ ትኩረት እየተመሩ የሚገኙ ተግባራት አፈጻጸም እየተሻሻለ መጥቷል፤
ነገር ግን ከመዋቅር ወደ መዋቅር የሚታዩ የአፈፃፀም ልዩነቶች አሁንም ማነቆ ሆነው ቀጥለዋል።
የአፈፃፀም ልዩነቶችን በማጥበብ፣ ውጤታማነትን ከፍ ለማድረግ በተጠያቂነት
መንፈስ መሥራት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ።
በበጀት ዓመቱ ቀሪ ጊዜ በሁሉም መስኮች ዕቅዶችን በተሟላ ሁኔታ
ለማሳካት መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።
የወልቂጤ ፣ የሆሳዕና፣ የሀላባ ቁሊቶ፣ የቡታጅራ እና የዱራሜ መሶብ _
የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ቀሪ ስራዎች በፍጥነት አጠናቅቆ፣
በጥቂት ቀናት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ
መቀጠሉንም ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) አመልክተዋል ።
በአጠቃላይ መሶብ _የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ዝግጁ ከማድረግ፣
የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባን፣ የኢትዮ _ኮደርስ ስልጠናን ፣ የገቢ አሰባሰብን ፣
የሥራ ዕድል ፈጠራን ከማጠናከር አኳያ ውጤታማ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ
መሆናቸው በመድረኩ ተለይቷል፤ተግባራቱ ተጠናክረው እንዲቀጥሉም
አቅጣጫ ተቀምጧል።
ከከተማና ከገጠር ኮሪደር ልማት አንፃር የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት
ሁሉም መዋቅሮች እንዲረባረቡ አቅጣጫ ተቀምጧል ።
የኑሮ ውድነትትን ለማረጋጋት የሚያግዙ ሁሉንም አማራጮች ተግባራዊ ማድረግ
እንደሚገባ ተመላክቷል ።
ከነዳጅ አቅርቦት አንፃር መሻሻሎች መታየታቸው የተገለፀ ሲሆን የነዳጅ
ስርጭቱን ከህገ ወጥ ሁኔታዎች በመከላከል ቅድሚያ ለሚያሻቸው ጉዳዮች
ቅድሚያ መስጠት በሚያስችል መልኩ እንዲመራ አቅጣጫ ተቀምጧል ።