Skip to main content

በሁሉም ዘርፎች በሚከናወኑ ተግባራት ተደማሪ ድሎች ለማስመዝገብ

መስራት ይገባል:-ርዕሰመስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና፣ሰኔ 7/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ

አፈጻጸም ማጠቃለያ ክልል አቀፍ የአመራር መድረክ

በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በሁሉም ዘርፍ ተደማሪ ድሎችን ለማስመዝገብ

በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

የቤተሰብ ብልጽግናን ማረጋገጥ ልዩልዩ አቅሞችን በማስተባበር የክልሉን

ብሎም የሀገሪቱን ልማት ቀጣይነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ መላው ህዝብ እና አመራሩ

 ላደረጉት የላቀ ድጋፍ ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።

ምርጫው ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሀዊ እንዲሆን ህብረተሰቡ የላቀ

ጥረት ማድረጉን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ኢትዮጵያ መርጣለች፣

አሸንፋለች ሲሉም አብራርተዋል።

የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ቀጣይነት ማረጋገጥ ተገቢ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ

በሁሉም መስክ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።

የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት ያለ እረፍት መስራት ይገባል ሲሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።

በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በጽናት በማለፍ የህዝብ ተጠቃሚነትን

ማረጋገጥ አብይ ጉዳይ በማድረግ መስራት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ

አስረድተዋል።

ያለንበት ዘመን እረፍት የሚሰጥ አይደለም ያሉት  ርዕሰ መስተዳድሩ

ለዚህም የአመራሩን ቁርጠኝነት ይጠይቃል ብለዋል።

ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሔድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩ እና ከምርጫ

በኋላ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለመዳፈር ጥረት ያደረጉ ኃይሎች እንደነበሩ

ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል።
ነገር ግን የነዚህ አካላት ሴራ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ድል መደረጉን ጠቅሰዋል።

ፈጥኖ ወደ መደበኛ ስራ ላይ ማተኮር ይጠበቃል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ

በመልዕክታቸው አስታውቀዋል።

Image