Skip to main content

 

በአጭር ጊዜ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈልገን በትብብር 

መስራት ብቻ ነው :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር 

ሆሳዕና፣ሰኔ 9/ 2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 

መርቀው ስራ አስጀምረዋል 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

ማዕከሉን መርቀው ስራ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት በአጭር 

ጊዜ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈልገን በትብብር መስራት 

ብቻ ነው ብለዋል። 

በክልሉ ከሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ በተለያዩ ከተሞች 

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን 

በመመረቅ ስራ ማስጀመር መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በቅርብ ቀን በሌሎች ከተሞች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 

ለምረቃ እንደሚበቁም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

በክልሉ የተያዘው በጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት ከ15 እስከ 17 

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ስራ ለማስጀመር 

እየተሰራ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። 

የሚያስፈልገው መተባበር ብቻ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከደባል 

አጀንዳ በመውጣት ለጋራ እድገት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። 

የሆሳዕና ከተማን ከሌሎች ትልልቅ ከተሞች ለማሰለፍ ከ3 እስከ 5 ዓመታት 

ብቻ በቂ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣የንጹህ መጠጥ ውሃ፣የንግድ ማዕከላት፣

ትምህርት ቤቶች፣የጤና ተቋማት እንዲሁም የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን 

ለማሟላት 10 ቢሊየን ብር በመመደብ መስራት ከተቻለ መሰረታዊ 

ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

የህዝብ ትብብር እና ድጋፍ ካለ አካባቢን መለወጥ እንደሚቻል የገለጹት 

ርዕሰ መስተዳድሩ የአካባቢው ተወላጆች እና የንግዱ ማህበረሰብ 

ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Image