admin11
Wed, 06/17/2026 - 11:19
መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀረቡለት የኢንቬስትመንት ልማት
ፕሮጄክት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ሆሳዕና ፣ሰኔ 9 ፣ 2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት
መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣
በቀረቡለት የተለያዩ የኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጄክት ጥያቄዎች
ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
በግብርና ፣በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች የኢንቬስትመንት
ልማት ፕሮጄክቶች ላይ ለመሠማራት 28 የኢንቬስትመንት ጥያቄዎች
ለመስተዳደር ምክር ቤቱ የቀረቡ መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን ፣ መስተዳድር
ምክር ቤቱ በቀረቡለት ፕሮጄክቶች ላይ ዝርዝር ውይይት ካደረገ በኋላ፣
የኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጄክቶቹ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገቡ
ውሳኔ አሳልፏል።
በኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጄክቶቹ የተመዘገው ካፒታል ከ3 ቢሊየን
9 መቶ 56 ሚሊየን በላይ ብር መሆኑ ተገልጿል ።
Image