Skip to main content
ርዕሰመስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከተረጂነትወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርትበጽ/ቤታቸው እየገመገሙ ነው

ርዕሰመስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት 

ከተረጂነትወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም 

ሪፖርትበጽ/ቤታቸው እየገመገሙ ነው 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 6/2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻውጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ ባለፉት 2 ዓመታት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት

 ለመሸጋገርየተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት እየገመገሙ ነው።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ባለፉት 2 ዓመታት በሀገር አቀፍም 

ሆነ በክልልአቀፍ ደረጃ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገር የሚያስችል 

ፕሮግራምበመቅረጽ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰው፤ 

የክልሉ መንግስት ለተከታታይ ሁለት ዓመታት በምግብ እራስን ለመቻል ዘርፈ 

ብዙ ጥረትሲያደርግ መቆየቱን ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክቷል። 

ከሚቀርበው ሪፓርት መነሻነት ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮችን በመለየት ዝርዝር 

ውይይትእንደሚደረግ አመላክተዋል።

Read more
የክልሉመስተዳደር ምክርቤት በአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀትአመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያየ፤ የቀጣይ ጊዜ ትኩረቶችንምአመላከተ

የክልሉመስተዳደር ምክርቤት በአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የ2018 

በጀትአመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያየ፤ የቀጣይ ጊዜ 

ትኩረቶችንምአመላከተ

ሆሳዕና፣ ሐምሌ 4/2018 ፦ 42 ተኛ መደበኛ ,ስብሰባዉን ያካሄደው 

የማዕከላዊኢትዮጵያ ክልል መስተዳደር ምክርቤት በክልሉ አስፈፃሚ 

መስሪያቤቶች የ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

ላይ ውይይትአድርጓል፤ የቀጣይ ጊዜ ትኩረቶችም ተመላክተዋል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ የክልሉ መንግሥት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች 

የእቅድአፈጻጸም በሁሉም የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የሰላምና ፀጥታ እና 

የመልካምአስተዳደር ዘርፎች ውጤታማና አበረታች እንደነበር በሪፖርቱ 

ተመላክቷል።

የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዓመታዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ሁኔታን

በተመለከተ፣ዓመታዊ ጠቅላላ ምርት ወይም የኢኮኖሚ ዕድገት በ10.2 

በመቶዓመታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ ተመላክቷል።

ጠቅላላ የክልሉ ዓመታዊ ምርትን በየክፍላተ ኢኮኖሚው አስመልክቶ 

በግብርናው ዘርፍ 8.1 በመቶ እድገት ማስመዝገብ መቻሉ በሪፖርቱ 

ተመልክቷል።

በኢንዱስትሪው ዘርፍ 21.8 በመቶ እድገት ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን 

በአገልግሎት ዘርፍ 10.5 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ 

በሪፖርቱ ተገልጿል።

በግብርናው ዘርፍ የታረሰ መሬት አድጓል፣ የሰብል ምርትና ምርታማነት አድጓል፣ 

የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ መጠን መጨመሩ እንዲሁም 

የአገልግሎትዘርፍ ዕድገትም መጨመሩ ተመላክቷል።

Read more
“በጎነት ከውስጥ መልካምነት የሚመነጭና ሀገርን ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሻግርታላቅ አገልግሎት ነው”፦ ርዕሠ መስተዳድር እንዳሻውጣሰው(ዶ/ር)

“በጎነት ከውስጥ መልካምነት የሚመነጭና ሀገርን ወደ ላቀ ከፍታ 

የሚያሻግርታላቅ አገልግሎት ነው”፦ ርዕሠ መስተዳድር 

እንዳሻውጣሰው(ዶ/ር)

ሆሳዕና፣ሐምሌ 3/2018 ፦"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ 

የሚንቀሳቀሰውሀገር አቀፍ የወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 

ቡድንበሆሳዕና ከተማ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በዕለቱ በተዘጋጀው የአቀባበል መረሐ ግብር ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ 

ክልልርዕሠ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለበጎ ፈቃደኞቹ የእንኳን 

ደህናመጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

“በጎነት ከውስጥ መልካምነት የሚመነጭና ሀገርን ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሻግር 

ታላቅአገልግሎት ነው ሲሉ ርዕሠ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ተናግረዋል።

በጎፈቃደኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ 'ፒስ ኮር' (Peace Corps) እና የ'ስካውት' 

ንቅናቄዎችያሉየረጅም ጊዜ ታሪካዊ መሠረቶች ያሉት መሆኑን አስታውሰዋል። 

ይህ መልካምእሴት በአሁኑ ወቅት ከለውጡ በኋላ በተከታታይና በተጠናከረ 

መልኩእየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ይህመርሃ ግብር የወደፊቷን ኢትዮጵያ የሚረከቡ ወጣቶች ማህበረሰባቸውንና 

ሀገራቸውንበቅርበት እንዲረዱ፣ እርስ በእርስ የዕውቀትና የባህል ልውውጥ 

እንዲያደርጉምቹዕድል የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል።

በሌሎች ሀገራት ሰዎች እስከ 70 እና 80 ዓመታቸው ድረስ በጉልበት ሀገራቸውን 

እንደሚያገለግሉበመጥቀስ፣ የሀገራችንም ወጣቶች የአገልግሎት ዘመናቸውን 

ማራዘምእንዲችሉ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።

አያይዘውም ከሀምሌ 28 ቀን ጀምሮ የሚካሄደውን ታሪካዊ ሀገራዊ ምክክር 

ወጣቶችበሀሳብና በሁሉም ረገድ እንዲደግፉ በጥብቅ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያውያን መክረውና ተስማምተው እንዲወጡ የበጎ ፈቃድ ቡድኑ አባላት 

የበኩላቸውንአዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሠ መስተዳድሩ በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ በጎ ፈቃደኞቹ  የመጡበትን 

መልካምየልማትና የአገልግሎት ዓላማ በተሳካ ሁኔታ እንዲወጡና ቆይታቸው 

የሰላምና ፍሬያማ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

Read more
የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አተገባበር በጠንካራ የአመራር ስርዓትና በቅርብ ክትትል ተመርቷል፤ የተሻሉ ውጤቶችም ተመዝግበዋል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር

የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አተገባበር በጠንካራ የአመራር ስርዓትና 

በቅርብ ክትትል ተመርቷል፤ የተሻሉ ውጤቶችም ተመዝግበዋል:- 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)

ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 3/2018፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የዞኖች እና የልዩ ወረዳዎችን የ2018 በጀት ዓመት 

ዕቅድ አፈጻጸም በጽሕፈት ቤታቸው ዛሬ ገምግመዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ እንደገለጹት፣የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ 

አተገባበር በጠንካራ የአመራር ስርዓትና በቅርብ ክትትል ተመርቷል፤ 

የተሻሉ ውጤቶችም ተመዝግበዋል። 


የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች 

በተቀናጀ መንገድ መመራቱም በጥንካሬ የሚጠቀስ መሆኑንም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አመልክተዋል።

ለተግባራቱ የተደረገው የድጋፍና የክትትል ሥራም የተጠናከረ መሆኑን ጠቅሰው፣ 

በሂደቱም በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋለል።

በሁሉም አካባቢዎች ሥራዎች በቅርብ ክትትል መመራታቸውን ያስታወቁት 

ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የግልና የጋራ ጥረቶችን በማቀናጀት እና የታዩ ክፍተቶችን 

በፍጥነት በማረም ውጤታማ ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በምርታማነትና በገቢ ማሳደግ ረገድ ጉልህ ውጤቶች 

መመዝገባቸውን ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው(ዶ/ር) ጠቁመው፣ የህብረተሰቡ 

ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን አስረድተዋል።

የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን አጀንዳ ማድረግ፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት፣ 

የገቢ አቅምን በሙሉ መጠቀም፣ ኢኒሼቲቮችን ማጠናከር፣ ምርታማነትንና 

የመረጃ ጥራትን ማሻሻል በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የህዝብ ተሳትፎን ማሳደግ፣ አመራሩና ሰራተኞች ሙሉ 

ሰዓታቸውን ለሥራ እንዲያውሉ ማድረግ እንዲሁም የህዝቦችን አንድነት 

ለማጠናከር ተከታታይነት ያላቸው ሥራዎችን ማከናወን ቀጣይ ትኩረት 

የሚሹ ጉዳዮች ስለመሆናቸውም አስገንዝበዋል።

Read more
ክቡር ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የዞንና ልዩ ወረዳ መዋቅሮችን የ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ዕቅድ አፈፃፀም እየገመገሙ ነው

ክቡር ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት 

የዞንና ልዩ ወረዳ መዋቅሮችን የ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ 

ዕቅድ አፈፃፀም እየገመገሙ ነው።

ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 3 /2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ 

መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) የክልሉን ዞኖችና ልዩ ወረዳ 

መዋቅሮች የ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ዕቅድ አፈፃፀም 

በጽህፈት ቤታቸው እየገመገሙ ይገኛሉ።

በክልሉ የሚገኙ የዞንና የልዩ ወረዳ አስተዳዳሪዎች የ2018 በጀት አመት 

የተጠቃለለ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን እያቀረቡ ይገኛል።

የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ 

ለ2019 በጀት አመት አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎም ይጠበቃል።

Read more
በክልሉ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በተሰራው ስራ ካለፉት ዓመታት የተሻለ ለውጥ ይጠበቃል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በክልሉ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በተሰራው ስራ 

ካለፉት ዓመታት የተሻለ ለውጥ ይጠበቃል - ርዕሰ 

መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 1/2018 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 3ኛውን ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር 

አቀፍ ፈተና በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት የፈተና አሰጣጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 

ከዚህ ቀደም ከምናውቀው የምዘና ዘዴዎች ወደ ዲጅታል በመለወጥ ላይ 

ይገኛል።

በክልላችንም በ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሚወስዱ 

ከአጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 61 በመቶው በበይነ-መረብ እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

ይሄም በክልል ባለፉት ዓመታት ከነበረው በበይነ መረብ ፈተና የመስጠት አቅም

በእጅጉ ያደገ ነው ብለዋል።

በሚቀጥለው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆችን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች 

በቂ ዝጅግት ተደርጎ ቁጥሩ ለማሳደግ ይሰራል ነው ያሉት።

በክልሉ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት ልዩ ልዩ ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹት 

ርዕሰ መስተዳድሩ የተማሪዎች የክፍል ውስጥ ምዘና ውጤት ከመከታተል ጀምሮ 

የውጤት ማሻሻያ ስልቶችን በመቅረጽ ተግባራዊ ስለመደረጉ ገልጸዋል።

በተለይም በክልሉ በተከታታይ ዓመት አንድም ተማሪ ማሳለፍ ካልቻሉ ትምህርት 

ቤቶች የማለፍ ተስፋ ያላቸው 886 ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ገብተው ልዩ የማጠናከሪያ 

ትምህርት እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

የእነዚህ ስራዎች ድምር ውጤት በተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር ላይ ለውጥ 

ያመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ተገኝተው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን አስጀምረዋል። ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 1/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ተገኝተው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዚህን ዙር ተፈታኞችን ፈተና በማስጀመር አበረታተዋል። ሀገር አቀፍ ፈተናው ከሰኔ 23 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት

ርዕሰመስተዳድርእንዳሻውጣሰው (ዶ/ር) በዋቸሞዩኒቨርስቲተገኝተው

የ12ኛክፍልሀገርአቀፍፈተናንአስጀምረዋል።

ሆሳዕና፣ሐምሌ 1/2018፦የማዕከላዊኢትዮጵያክልልርዕሰመስተዳድር

እንዳሻውጣሰው (ዶ/ር) በዋቸሞዩኒቨርስቲተገኝተው የ12ኛክፍልሀገር

አቀፍፈተናየዚህንዙርተፈታኞችንፈተናበማስጀመርአበረታተዋል።


ሀገርአቀፍፈተናውከሰኔ 23 ቀን 2018 ዓመተምህረትጀምሮበተለያዩዙሮች

እየተሰጠመሆኑየሚታወስሲሆን፤ለተፈጥሮሳይንስተማሪዎችበሶስትዙሮች

እናለማህበራዊሳይንስተማሪዎችምበተተመሳሳይበሶስትዙሮችእየተሰጠ

መሆኑተገልጿል።

የ12ኛክፍልሀገርአቀፍፈተናአጀማመሩላይምክትልርዕሰመስተዳድርእና

የማህበራዊክላስተርአስተባባሪአቶአንተነህፍቃዱእናየዋቸሞዩኒቨርስቲ

የማኔጅመንትአባላትተገኝተዋል።

ሆሳዕና፣ሐምሌ 1/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ተገኝተው የ12ኛ ክፍል ሀገር

-አቀፍ ፈተና የዚህን ዙር ተፈታኞችን ፈተና በማስጀመር አበረታተዋል።


ሀገር-አቀፍ ፈተናው ከሰኔ 23 ቀን 2018 ዓመተ-ምህረት ጀምሮ በተለያዩ ዙሮች

እየተሰጠ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፤ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሶስት ዙሮች

እና ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችም በተተመሳሳይ በሶስት ዙሮች እየተሰጠ

መሆኑ ተገልጿል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር-አቀፍ ፈተና አጀማመሩ ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና

የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አንተነህ ፍቃዱ እና የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ

የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በቡታጅራ ከተማ ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በቡታጅራ ከተማ 

ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ 

ሆሳዕና፣ሰኔ 30/2018 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ ከሰንበት 

እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀምረዋል 

በቡታጅራ ከተማ የተገነባው ከሰንበት እስከ ሰንበት የግብይት ማዕከል 

15 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል። 

የግብይት ማዕከሉ ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሲሆን 

አምራቹን እና ሸማቹን ማህበረሰብ በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነቱን 

በማረጋጋት ረገድ የጎላ ሚና እንዳለውም ተጠቁሟል። 

በማዕከሉ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት ቀርቦ ግብይት 

እየተካሔደበት ነው።

 

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በቡታጅራ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በቡታጅራ ከተማ 

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ 

ሆሳዕና ፣ ሰኔ 30/2018፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በቡታጅራ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል 

አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ 

በማዕከሉ በመጀመሪያ ዙር በ6 ተቋማት 22 አገልግሎት እየተሰጠ 

መሆኑም ተመላክቷል። 

በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልኡክ በማዕከሉ እየተሰጠ ያለውን 

አገልግሎት ተመልክተዋል።

Read more
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዘንድሮው ክልል አቀፍ የተቀናጀ የመኸር ግብርና ልማት ንቅናቄ ከቀናት በፊት በይፋ ተጀምሯል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዘንድሮው ክልል አቀፍ የተቀናጀ 

የመኸር ግብርና ልማት ንቅናቄ ከቀናት በፊት በይፋ ተጀምሯል። 

ከዝናቡ ሁኔታ ጋርም የተያያዙ ስጋቶች በተወሰነ ደረጃ እየተፈቱ ይመስላል፤

ሁሉንም ዕድሎች፣አቅሞችና ፀጋዎች አጣጥሞ፣መኸሩን ለተሻለ ምርታማነት 

መጠቀም ይጠበቃል።

Read more