ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ(ዶ/ር ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተመሠረተበትን ሁለተኛ ዓመት አስመልክተዉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ የመልዕታቸዉም ሙሉ ይዘት የሚከተለዉ ነዉ፦

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ(ዶ/ር )  የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተመሠረተበትን ሁለተኛ ዓመት አስመልክተዉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ የመልዕታቸዉም ሙሉ ይዘት የሚከተለዉ ነዉ

ለመላዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች፣

 ክልላችን ለተመሠረተበት ሁለተኛ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ!አደረሰን !

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተመሠረተበት  ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓመተ ምህረት እነሆ ሁለት ዓመት ሆነዉ። 

እነዚህ ሁለት የትግልና የስኬት ዓመታት ፦በሁሉም መስኮች ተጨባጭ ዉጤቶች የተመዘገቡባቸዉ ፣በየምዕራፉ ካገጠሙ ፈተናዎች ትምህርት የተወሰደባቸዉ፣ የሕዝቦች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ የመጣባቸዉ፣ ሠላማዊ ፣ ጠንካራና ምሳሌ ሊሆን የሚችል ክልል ለመፍጠር የሚያስችሉ ምቹ መደላድሎች እዉን የሆኑባቸዉ፣ 

message of the Presidant2

Message of The President

Message from His excellency Dr. Endashaw Tassew - President of Central Ethiopia Regional state 

የርዕሰ መስተዳድሩ መልእክት

                   የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው መልዕክት፡-               

His Excellence Dr endashaw Tassewየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስትን ከመሰረቱ የክልል መንግስታት አንዱ ነው፡፡የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከቀድሞው የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ተለይቶ ራሱን ችሎ ክልል ሆኖ አንዲደራጅ በሪፈረንደም -በህዝበ ውሳኔ መወሰኑን ተከትሎ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም ራሱን ችሎ ነሀሴ 13  ቀን 2015 ዓመተ ምህረት ላይ የህዝቦች ይሁንታንና  የህገ መንግስት ማሻሻያን  መሰረት አድርጎ የተደራጀ ክልላዊ መንግስት ነው፡፡

 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የሀዲያ፣ የስልጤ ፣ የከምባታ፣ የሀላባ ፣ የጠምባሮ፣ የየም፣ የማረቆ፣ የቀቤና እና የዶንጋ  ብሄር፣ ብሄረሰቦችን እና ሌሎችንም ህዝቦች በማቀፍ የተደራጀ ክልል ነው፡፡ ክልሉ በሰባት ዞኖች ፡-ሀዲያ ፣ጉራጌ፣ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ከምባታ፣ ሀላባና የም ዞኖች እና በሶሰት ልዩ ወረዳዎች ፡- ጠምባሮ ፣ ማረቆና ቀቤና ልዩ ወረዳዎች በማቀፍ የተዋቀረ ነው፡፡

 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጋራ እሴቶች የተሳሰረች፣ በጋራ ትርክት  የጸናች፣ በጋራ ህልም ተስፋዋን ከፍ  ለማድረግ የምትተጋ ህብረ - ብሄራዊት ኢትዮጵያን በመገንባቱ ሂደት የበኩላቸውን ለመወጣት ከወትሮው በላቀ የታታሪነት እና የስራ ፈጣሪነት መንፈስ ለመንቀሳቀስ ቃላቸውን አድሰው ተነስተዋል፡፡ 

በህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም ስርዓቱ የተደነገጉ የራስ አስተዳደር እና የጋራ አስተደዳደር ማዕቀፎችን መሰረት አድርጎ በመንቀሳቀስ ፣ ማንነት እና ኢትዮጵያዊ አንድነት ሚዛናቸውን ጠብቀው የሚራመዱባት ኢትዮጵያን እውን በማድረጉ ሂደት የእያንዳንዳችን ድርሻ ወሳኝ በመሆኑ መላው ዜጎች የየበኩላቸውን አንዲያበረክቱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

ዘላቂ ሰላም ፣ ለዘላቂ ልማት እና ለዘላቂ ሀገር ግንባታ መሰረት በመሆኑ መላው ህዝባችን ሰላሙን ለማጽናት፣ ልማቱን ለማፋጠን በቁርጠኝነት እና በጋራ መረባረብ በሚጠበቅበት ወቅት ላይ መሆኑንም ለማስታወስ እወዳለሁ፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የመልሚያ አቅሞችና ጸጋዎች ባለቤት የሆነች ብሩህ ተስፋ ያላት ሀገር ናትና የምግብ  ዋስትና ሉዓላዊነትን በጋራ ትጋት እውን በማድረግ ሉዓላዊነቷ እና ብሄራዊ ክብሯ የተሟላ አንዲሆን የጀመርነውን ጥረት እናጠናክር! ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ የምትከበር እና የምትፈራ ሀገር እንድትሆን በሁሉም መስኮች ርብርብ እናድርግ!

                                                                 አመሰግናለሁ!

Latest News

Services

Office of the President and The State Council 
Office of The Advisors 
Law and Good Governance Affairs
GERD Coordination Project Office 

You May Have Missed

Media and Pages

                                                                     our media and page