admin11
Wed, 11/25/2026 - 14:42
ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አሥራት (ዶ/ር) በተገኙበት መሶብ
የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና የፋይዳ መታወቂያ ኢሼቲቮች
አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው።
ሆሳዕና፣ ህዳር 16/2019፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
የትምጌታ አሥራት(ዶ/ር) እና ሌሎችም የክልሉ፣የዞንና ልዩ ወረዳ ከፍተኛ
አመራሮች በተገኙበት የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 አካል የሆኑት መሶብ
የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና የፋይዳ መታወቂያ ሀገራዊ ኢሼቲቮች
አፈጻጸም ግምገማ በሆሳዕና ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።
በመድረኩ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የህዝቡን አገልግሎት በማሳለጥ
ያመጣቸው ለውጦች፣ መቀረፍ ያለባቸው ችግሮች፣ በፋይዳ መታወቂያ ረገድ
ደግሞ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ሆነው የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ
ለማድረግ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች የሚገመገሙ ይሆናል።
Image