በክልሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነትን
ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት ውጤታማ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች
ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ
ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት
ጊዜ እንደገለጹ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነትን
ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት ውጤታማ ነው ብለዋል።
በሁሉም የምርት ወቅቶች 1ሚሊየን 259ሺ 472 ሄ/ር መሬት በማልማት
ከ160 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ተገኝቷል ብለዋል።
በመኸር እርሻ በአዝርዕትና በሆርቲካልቸር ከ57ሚሊየን 547ሺ ኩንታል
በላይ ምርት መገኘቱን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቁመዋል።
በክልሉ በበልግ የአዝመራ ወቅት 267ሺ 817 ሄ/ር ማሳ በማልማት ከ12 ነጥብ
5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ስመገኘቱም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
በአዝርዕትና በሆርቲካልቸር ስብሎች 437ሺ 182 ሄ/ር ማሳ በማልማት ከ 62
ሚሊየን ,872 ሺ ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ ተችሏል ሲሉም ርዕሰ
መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል።
በክልሉ በአትክልት በቅባትና በስራስር ሰብሎች የላቀ ውጤት መመዝገቡን
ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በምርት ዘመኑ በኩታ ገጠም እርሻ ከ6ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት
መሰብሰብ መቻሉንም ጠቅሰዋል።
በፀደይ ወቅት እርሻ 63ሺ540 ሄክታር መሬት በማልማት ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን
በላይ ኩንታል ምርት ተሰብስቧል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው
ጠቅሰዋል።
በክልሉ በበጋ መስኖ ልማት ከ37 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ስለመገኘቱም
አብራርተዋል።