Skip to main content

በክልሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነትን 

ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት ውጤታማ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች 

ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ 

ከተማ እየተካሔደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት 

ጊዜ እንደገለጹ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነትን 

ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት ውጤታማ ነው ብለዋል። 

በሁሉም የምርት ወቅቶች 1ሚሊየን 259ሺ 472 ሄ/ር መሬት በማልማት

ከ160 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ተገኝቷል ብለዋል። 

በመኸር እርሻ በአዝርዕትና በሆርቲካልቸር ከ57ሚሊየን 547ሺ ኩንታል 

በላይ ምርት መገኘቱን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቁመዋል። 

በክልሉ በበልግ የአዝመራ ወቅት 267ሺ 817 ሄ/ር ማሳ በማልማት ከ12 ነጥብ 

5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ስመገኘቱም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

በአዝርዕትና በሆርቲካልቸር ስብሎች 437ሺ 182 ሄ/ር ማሳ በማልማት ከ 62 

ሚሊየን ,872 ሺ ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ ተችሏል ሲሉም ርዕሰ 

መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል። 

በክልሉ በአትክልት በቅባትና በስራስር ሰብሎች የላቀ ውጤት መመዝገቡን 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በምርት ዘመኑ በኩታ ገጠም እርሻ ከ6ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት 

መሰብሰብ መቻሉንም ጠቅሰዋል። 

በፀደይ ወቅት እርሻ 63ሺ540 ሄክታር መሬት በማልማት ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን 

በላይ ኩንታል ምርት ተሰብስቧል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው 

ጠቅሰዋል።

በክልሉ በበጋ መስኖ ልማት ከ37 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ስለመገኘቱም 

አብራርተዋል።

Image