admin11
Mon, 06/15/2026 - 09:29
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) በወልቂጤ ከተማ
በያበሩስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና አስጀመሩ
ሆሳዕና ፣ ሰኔ 8/2018 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በወልቂጤ ከተማ በያበሩስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና አስጀመሩ
በተያዘው የትምህርት ዘመን ከሰኔ 8 እስከ 12 / 2018 ባሉት ቀናት
የ6ኛ እና የ8 ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ይሰጣል።
ይህን ተከትሎም በዛሬው እለት የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና
በተለያዩ ማዕከላት እየተሰጠ ነው።
በክልሉ 46ሺ 151 ወንዶች እንዲሁም 45ሺ 767 በድምሩ
91ሺ 918 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተና ይወስዳሉ።
Image