Skip to main content
ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) የስራ ርክክብ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) የስራ ርክክብ አደረጉ 

ሆሳዕና፣መስከረም 27/2019፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ 

መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ከቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው( ዶ/ር ) ጋር የስራ ርክክብ አደረጉ 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) 

ከቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ጋር በጽ/ቤታቸው 

የስራ ርክክብ አድርገዋል። 

የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት 

ባለፉት ሶስት ዓመታት ክልሉ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ በማለፍ ውጤታማ 

ስራ ማከናወን መቻሉን አብራርተዋል። 

ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ፕሮጀክቶች 

ተግባራዊ መደረጉን በአብነት ጠቅሰዋል።

ባለፉት ሶስት ዓመታት ሰርተን ያሳካናቸው ፣ ጀምረን ያላጠናቀቅናቸው ጉዳዮች 

እንዲሁም በረጅም ጊዜ አቅደን የጀመርናቸው ስራዎች አሉ ሲሉም ዶ/ር እንዳሻው 

ጠቁመዋል። 

በቅብብሎሽ ሂደት ውስጥ ስራን ጀምሮ ማጠናቀቅ ተገቢ ነው ያሉት ዶ/ር እንዳሻው 

የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉንም አካላት ቁርጠኝነት ይጠይቃል 

ብለዋል። 

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ከምስረታ እስከ አሁን የነበረው ጉዞ፣የክልሉ መንግስት 

የ2019 በጀት አመት እቅድ እንዲሁም የክልሉን መንግስት የሰባት ዓመታት መሪ 

እቅድ ለአዲሱ ርዕሰ መስተዳድር አስረክበዋል።

ለአዲሱ ርዕሰ መስተዳድር መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል። 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በበኩላቸው 

በሀገሪቱ ከውስጥም ሆነ ከውጭ እያጋጠመ ያለውን የጠላት ሴራ በማክሸፍ የመደመር 

መንግስት እውን መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

አዲስ ክልል መስርት፣ተቋም አደራጅቶ፣የሰው ሀይል በማሰማራት፣የክልሉን 

ህዝብ አንድነት ጠብቆ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እድለኝነት ነው ሲሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

የክልሉ መንግስት አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ማብቃት የቻለ ክልል 

መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል። 

ስልጣን የግል ጥቅም መገልገያ ሳይሆን ህዝብ የምናገለግልበት፣ሀገር የምንገነባበት 

ትልቅ ኃላፊነት ስለመሆኑም አስረድተዋል።

ህዝብ የሰጠንን አደራ በቁርጠኝነት ለመወጣት ጥረት እናደርጋለን ሲሉም 

አስረድተዋል።

Read more
ህብረ-ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ ሁለንተናዊ ሉአላዊነቷ የተከበረ የማትበገር ሀገር መገንባት ይጠበቅብናል:- ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)

ህብረ-ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ ሁለንተናዊ ሉአላዊነቷ 

የተከበረ የማትበገር ሀገር መገንባት ይጠበቅብናል:- 

ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) 

ሆሳዕና፣መስከረም 23/2019 ዓ.ም ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ 

ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ ዙር መስራች 

ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት 

(ዶ/ር) እንደገለጹት በምክር ቤቱ ፊት ቆሜ የተሰጠኝን የህዝብ 

አደራ እና ኃላፊነት በከፍተኛ ትህትና በጥልቅ አክብሮት እና 

በንጹህ የአገልጋይነት ስሜት ነው ብለዋል። 

ብልጽግና ፓርቲ፣መንግስት እና የክልሉ ህዝቦች ለጣሉብኝ እምነት 

እና ለተሰጠኝ ኃላፊነት አክብሮታዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

ሀገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 

ህዝቦቿም እንዲሁ ታላቅ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። 

የአኩሪ ታሪክ፣ቅርስ፣ባህል፣ትውፊት፣የእምነት፣የድንቅ ማንነት፣

የበርካታ የገጸ ምድር እና የገጸ ምድር ኃብት ባለቤት ስለመሆናችን 

ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል። 

ፈጣሪ የቸረንን አቅም፣ጉልበት እና ጸጋ ወደ ሀገራዊ ጥቅም በመቀየር 

የባህር በር ጥያቄአችንን እልባት ሰጥተን የህዝባችንን ሁለንተናዊ 

ብልጽግናን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያን ስልጣኔ መልሰን መገንባት እና 

ለመላው አፍሪካ ምሳሌ መሆን ይኖርብናል ብለዋል። 

ብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ግልጽ ራዕይ አለው 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ህብረ ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ ሁለንተናዊ 

ሉአላዊነቷ የተከበረ የማትበገር፣በስፋት የምታመርት፣የጸናች ኢትዮጵያን 

መገንባት ነው ብለዋል። 

የክልላችን መንግስት ራዕይ እና ተልዕኮ የዚሁ ነጸብራቅ ስለመሆኑም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።

Read more
ምክር ቤቱ አቶ አንተነህ ፍቃዱን በድጋሚ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/አስተዳደር አድርጎ ሰየመ

ምክር ቤቱ አቶ አንተነህ ፍቃዱን በድጋሚ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ 

ክልል ም/አስተዳደር አድርጎ ሰየመ 

ሆሳዕና፣መስከረም 23/2019 ዓ.ም ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ

ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ ዙር መስራች 

ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 

አቶ አንተነህ ፍቃዱን በድጋሚ የክልሉ ም/አስተዳደርና 

የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል። 

አቶ አንተነህ ፍቃዱ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ

ፈፅመዋል።

Read more
ምክር ቤቱ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አድርጎ ሰየመ

ምክር ቤቱ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር የክልሉ መንግስት ዋና 

ተጠሪ አድርጎ ሰየመ 

ሆሳዕና፣መስከረም 23/2019 ዓ.ም ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ 

ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ ዙር መስራች 

ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 

ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አድርጎ

ሾሟል። 

ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ 

በመፈጸም ስራ ጀምረዋል።

Read more
የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ

የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ 

ሆሳዕና ፣መስከረም 23፣ 2019 ዓ.ም ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ 

ክልል ምክር ቤት 7ኛ ዙር መስራች ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ 

እያካሄደ ይገኛል፡፡ 

ምክር ቤቱ በጉባዔው የትምጌታ አስራትን (ዶ/ር) የማዕከላዊ 

ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሰይሟል፡፡

Read more
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ክብርት ወ/ሮ ነይማ ሙኒር ዋና አፈ ጉባዔ አድርጎ ሰየመ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ክብርት ወ/ሮ ነይማ 

ሙኒር ዋና አፈ ጉባዔ አድርጎ ሰየመ

ሆሳዕና ፣ መስከረም 23/2019 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 

1ኛ መደበኛ ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ነይማ ሙኒር የምክር ቤቱ ዋና 

አፈ-ጉባዔ አድርጎ ሰይሟል።

Read more
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ ዙር መስራች ጉባዔ በወልቂጤ ከተማ መካሄድ ጀምሯል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 

7ኛ ዙር መስራች ጉባዔ በወልቂጤ ከተማ መካሄድ ጀምሯል 

ሆሳዕና ፣ መስከረም 23 / 2019 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ 

ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ ዙር መስራች ጉባዔ 

በወልቂጤ ከተማ መካሄድ ጀምሯል 

በጉባኤው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ የአስፈጻሚ 

አካላት ሹመት እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

Read more
ባለፉት ዓመታት በክልሉ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ባለፉት ዓመታት በክልሉ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት 

የማረጋገጥ ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል:-ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና፣መስከረም 22/2019 ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ 

ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአሰራር እና የስነ-ምግባር ደንብ ላይ 

በወልቂጤ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው 

(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት መንግስት እና 

ፓርቲ ያስቀመጧቸውን መንታ ግቦች ማሳካት የሚያስችል አቅም 

መፈጠሩን ተናግረዋል። 

ሰላማዊ ምርጫ በማካሄድ ለህዝቡ ፖሊሲዎቻችንን በአማራጭነት 

አቅርበን አሸናፊ የመሆን ግባችንን አረጋግጠናል ብለዋል። 

ከሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌባለው 

መዋቅር ውጤታማ ስራ ማከናወን ተችሏል ብለዋል።

በክልሉ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ልዩ ትኩረት 

እንደተሰጠውም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

የክልሉን የሶስት አመታት ጉዞ ለምክር ቤት አባላት ግንዛቤ ማስጨበጥ 

ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል። 

ምክር ቤቱ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ስራዎችን ሲያከናውን ተደማሪ 

ጉዳዮችን እንዲለይ እና አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን በተገቢው ሁኔታ 

እንዲያግዝ ያስችላል ብለዋል። 

የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስትን ስራ እንዴት ይቆጣጠር

እንደነበር እና የድጋፍ እና ክትትል ስራ ላይ የጋራ ተግባቦት መፍጠር 

የሚያስችል መድረክ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው( ዶ/ር) በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ7ተኛ ዙር የምርጫ ዘመን ለተመረጡ አዲስ የምክር ቤት አባላት በወልቂጤ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው( ዶ/ር) በተገኙበት 
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ7ተኛ ዙር የምርጫ ዘመን 

ለተመረጡ አዲስ የምክር ቤት አባላት በወልቂጤ ከተማ 

ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል 

ሆሳዕና፣መስከረም 22/2019፦ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአሰራር እና የስነ-ምግባር 

ደንብ ላይ በወልቂጤ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

Read more
አዲሱ 2019 _ በሀገር አቀፍ ደረጃ እና በክልሉ የጀመርናቸው የልማት ስራዎች የሚሳኩበት ብሩህ ጊዜ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር

አዲሱ 2019 _ በሀገር አቀፍ ደረጃ እና በክልሉ የጀመርናቸው 

የልማት ስራዎች የሚሳኩበት ብሩህ ጊዜ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር

 እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር 

ሆሳዕና፣መስከረም 12/2019)ለ 'ያሆዴ '_የሀዲያ ብሔር ዘመን 

መለወጫ በዓል በሀዲይ ነፈራ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል። 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ለበዓሉ ታዳሚዎች ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ያሆዴ በዓል 

ከረጅም ድካምና ልፋት በኋላ መላው ማህበረሰባችን በጉጉት የሚጠብቀው 

እና ህብረተሰቡ በጋራ ተገናኝቶ ዘመድ የሚጠይቅበት ሌሎች መልካም 

እሴቶቻችን ጎልተው የሚታዩበት ነው ብለዋል። 

የመስከረም ወር ለክልሉ ማህበረሰብ የደስታ ጊዜ ነው ያሉት ርዕሰ 

መስተዳድሩ በተለይም ለሀዲያ ብሔረሰብ የተለየ ስለመሆኑም 

አመላክተዋል። 

የክረምቱ ወቅት ጨለማ አሊያም ጭጋግ ሳይሆን ይህ ጊዜ ፈጣሪ 

ያስቀመጠው ውብ ጊዜ መሆኑን ጠቁመዋል።

ክረምትን፣በጋን፣ጸደይን ብሎም በልግን ለሰጠን ፈጣሪ ምስጋና ይገባል 

ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

ያሆዴ በዓልን ስናከብር ስለ ሀገራችን ሰላም አንድነት፣ስለ ህዝቦች መፈቃቀር 

ስለመከባበር፣የሰላም እና የልማት ጉዳዮችን አጣምረን ነው ብለዋል። 

ያሆዴን በአል ከዚህም በላይ በድምቀት ለማክበር መዘጋጀት ይኖርብናል 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በአሉን ተሰባስበን 

ያከበርንበት ሁኔታ የተለየ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

ከሀገር ውጪ ያሉ ተወላጆች ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው በዓሉን ሲያከብሩ ስለ 

ልማት፣ስለ ሰላም፣ስለ ቤተሰብ ስለ ባህላችን የሚመካከሩበትን እድል 

እንደሚፈጥርም አስረድተዋል።

2019 ዓ/ም ለኢትዮጵያ ብሩህ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ብዙ ችግሮቻችንን 

የምንሻገርበት፣በሀገር አቀፍ ደረጃ እና በክልሉ የጀመርናቸው የልማት ስራዎች 

የሚሳኩበት ስለመሆኑም አመላክተዋል። 

ዓመቱ የህዝባችንን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የምናሳድግበት ነው ብለዋል። 

ፕሮግራሙ እንዲሳካ በገንዘብ በሙያ በእውቀት እና በልዩ ልዩ መስክ ተሳትፎ 

ላደረጉ አካላት ርዕሰ መስተዳድሩ አመስግነዋል። 

ያሆዴ የሰላም የፍቅር፣ህዝብን የማገልገል እና የይቅርታ በዓል እንዲሆን 

ርዕሰ መስተዳድሩ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

Read more