እንኳን ወደ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ኦፊሻላዊ ድረ-ገጽ በድህና መጡ
Message of The President
Message from His excellency Dr. Endashaw Tassew - President of Central Ethiopia Regional state
የርዕሰ መስተዳድሩ መልእክት
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው መልዕክት፡-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስትን ከመሰረቱ የክልል መንግስታት አንዱ ነው፡፡የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከቀድሞው የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ተለይቶ ራሱን ችሎ ክልል ሆኖ አንዲደራጅ በሪፈረንደም -በህዝበ ውሳኔ መወሰኑን ተከትሎ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም ራሱን ችሎ ነሀሴ 13 ቀን 2015 ዓመተ ምህረት ላይ የህዝቦች ይሁንታንና የህገ መንግስት ማሻሻያን መሰረት አድርጎ የተደራጀ ክልላዊ መንግስት ነው፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የሀዲያ፣ የስልጤ ፣ የከምባታ፣ የሀላባ ፣ የጠምባሮ፣ የየም፣ የማረቆ፣ የቀቤና እና የዶንጋ ብሄር፣ ብሄረሰቦችን እና ሌሎችንም ህዝቦች በማቀፍ የተደራጀ ክልል ነው፡፡ ክልሉ በሰባት ዞኖች ፡-ሀዲያ ፣ጉራጌ፣ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ከምባታ፣ ሀላባና የም ዞኖች እና በሶሰት ልዩ ወረዳዎች ፡- ጠምባሮ ፣ ማረቆና ቀቤና ልዩ ወረዳዎች በማቀፍ የተዋቀረ ነው፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጋራ እሴቶች የተሳሰረች፣ በጋራ ትርክት የጸናች፣ በጋራ ህልም ተስፋዋን ከፍ ለማድረግ የምትተጋ ህብረ - ብሄራዊት ኢትዮጵያን በመገንባቱ ሂደት የበኩላቸውን ለመወጣት ከወትሮው በላቀ የታታሪነት እና የስራ ፈጣሪነት መንፈስ ለመንቀሳቀስ ቃላቸውን አድሰው ተነስተዋል፡፡
በህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም ስርዓቱ የተደነገጉ የራስ አስተዳደር እና የጋራ አስተደዳደር ማዕቀፎችን መሰረት አድርጎ በመንቀሳቀስ ፣ ማንነት እና ኢትዮጵያዊ አንድነት ሚዛናቸውን ጠብቀው የሚራመዱባት ኢትዮጵያን እውን በማድረጉ ሂደት የእያንዳንዳችን ድርሻ ወሳኝ በመሆኑ መላው ዜጎች የየበኩላቸውን አንዲያበረክቱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡
ዘላቂ ሰላም ፣ ለዘላቂ ልማት እና ለዘላቂ ሀገር ግንባታ መሰረት በመሆኑ መላው ህዝባችን ሰላሙን ለማጽናት፣ ልማቱን ለማፋጠን በቁርጠኝነት እና በጋራ መረባረብ በሚጠበቅበት ወቅት ላይ መሆኑንም ለማስታወስ እወዳለሁ፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የመልሚያ አቅሞችና ጸጋዎች ባለቤት የሆነች ብሩህ ተስፋ ያላት ሀገር ናትና የምግብ ዋስትና ሉዓላዊነትን በጋራ ትጋት እውን በማድረግ ሉዓላዊነቷ እና ብሄራዊ ክብሯ የተሟላ አንዲሆን የጀመርነውን ጥረት እናጠናክር! ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ የምትከበር እና የምትፈራ ሀገር እንድትሆን በሁሉም መስኮች ርብርብ እናድርግ!
አመሰግናለሁ!
የቅርብ ጊዜ ዜና
በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት ያጋጠሙ ፈተናዎችን በሰከነ እና በበሳል
የአመራር ጥበብ በመሻገር ወደ …
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ባለፉት ሁለት
ዓመታት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት …
ጂኮ ፓርክ ክልሉን ከማስተዋወቅ ባለፈ ከቱሪዝም
ኢንዱስትሪው የሚገኘውን ሀብት ያሳድጋል:-…
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምልከታ …
ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በጤና ተቋማት እየተሰጠ
ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል የክልሉ መንግስት …
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) መልዕክት …
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የቡታጅራ ከተማ
የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ …
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )የሆሳዕና ከተማ
የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ሂደት …
አገልግሎቶች




አምልጦዎት ይሆን
ሚዲያ እና ገጽ
our media and page