Skip to main content
በክልሉ በገቢ እና በንግድ ስርዓቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት አስገዳጅ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር

በክልሉ በገቢ እና በንግድ ስርዓቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት 

አስገዳጅ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል:- 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር 

ሆሳዕና፣ነሐሴ 4/2018፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ እና 

የክልሉ የንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ የህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር፣ ኑሮ 

ማረጋጋት እና የታክስ ህግ ተገዢነት ለማረጋገጥ የተዘጋጀ የምክክር 

መድረክ እየተካሄደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

በምክክር መድረኩ እንደገለጹት በክልሉ በገቢ እና በንግድ ስርዓቱ ላይ 

መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት አስገዳጅ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ትኩረት 

ማድረግ ይገባል ብለዋል። 

በክልሉ በገቢ እና በንግድና ገበያ ልማት ሴክተሮች ወቅታዊ አጀንዳ ላይ 

በመወያየት ለቀጣይ ስራ ተግባቦት መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል። 

የልማት ስራዎቻችንን ስኬታማ ለማድረግ የመወያየት እና የመመካከር 

ባህል እያደገ መጥቷል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። 

የታክስ ህግን ማስከበር እና ገቢን ማሳደግ ላይ የጋራ ጥረት ይጠይቃል ያሉት 

ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱ 

በሶስት መቶ በመቶ አድጓል ብለዋል።ነገር ግን የክልሉ ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው 

ገቢ አንጻር አሁንም ቀሪ ስራ እንዳለ አመላክተዋል። 

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በአመት በአማካይ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱን ከ15 

እስከ 20 ቢሊየን በማሳደግ የክልሉን ገቢ የማመንጨት አቅም ከ120 ቢሊየን ብር 

በላይ ከፍ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል። 

በአምስት ዓመታት ውስጥ በዘርፉ ጠንክረን የምንሰራ ከሆነ የክልሉን ገቢ በ200 

ቢሊየን ብር ማሳደግ እንደሚቻልም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። 

የገቢ አሰባሰብ ስርዓት እያደገ ሲሄድ የክልሉን ከተሞች የመሰረተ ልማት ፍላጎት 

ማሟላት እንደሚያስችልም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

የክልሉን ከተሞች በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ማሳደግ የሚያስችል አዲስ 

እቅድ ማዘጋጀት ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በክልሉ በየአመቱ ከ10 እስከ 15 ቢሊየን ብር ከደረሰኝ ገቢ ብቻ መሰብሰብ 

እንደሚቻል ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

በየጊዜው እያደገ ለመጣው የህዝብ የልማት ፍላጎት ምላሽ መስጠት የሚቻለው 

ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ሲቻል ብቻ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው 

ጠቅሰዋል። 

በክልሉ የንግድ ስርዓቱን መቆጣጠር እና መስመር ማስያዝ ይገባል ያሉት ርዕሰ 

መስተዳድሩ በሀገሪቱ የሚወጡ ደንቦች እና መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ 

አስፈላጊ ስለመሆኑም ጠቁመዋል። 

በንግድ እና በገቢ ሴክተሮች እያጋጠመ ያለውን ችግር በመፍታት ረገድ የላቀ 

ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እያጋጠመ ያለውን የዋጋ ንረት መቆጣጠር ተገቢ ነው 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ 

በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል። 

በክልሉ ያሉትን ጸጋዎች በማልማት ምርታማነትን ማሳደግ የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር 

ረገድ ጉልህ አበርክቶ እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በክልሉ አስገዳጅ የሆ የህግ ማስከበር ስራ ላይ በልዩ ትኩረት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ጥቂቶች ብቻ የሚዘውሩት የንግድና የገቢ ስርዓት ሊኖር 

አይገባም ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

Read more
ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነ ጠንካራ ስራ የክልሉን ገቢ የመሰብሰብ አቅም 35 ቢሊየን ብር ማሳደግ ተችሏል:- 

ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነ ጠንካራ ስራ የክልሉን ገቢ የመሰብሰብ 

አቅም 35 ቢሊየን ብር ማሳደግ ተችሏል:- 

ሆሳዕና፣ነሐሴ 4/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ እና የክልሉ 

የንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ የህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር፣ ኑሮ ማረጋጋት እና 

የታክስ ህግ ተገዢነት ለማረጋገጥ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በመድረኩ

መክፈቻ እንደገለጹት የገቢ እና የንግድና ገበያ ልማት ሴክተሮች በኢኮኖሚ ዘርፍ 

እና ኑሮን በማረጋጋት ረገድ የላቀ ሚና አላቸው ብለዋል። 

ክልሉ ስራ ሲጀምር የገቢ ሴክተሩ የሚያመነጨው ገቢ ከ8 ቢሊየን ብር በላይ እንዳልነበር 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ለዘርፉ በተሰጠ ትኩረት ይህን አሀዝ ከ8 ወደ 35 ቢሊየን 

ብር ማሳደግ ስለመቻሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል። 

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በአመት በአማካይ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱን ከ15 እስከ 

20ቢሊየን በማሳደግ የክልሉን ገቢ የማመንጨት አቅም ከ120 ቢሊየን ብር በላይ ከፍ 

ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል። 

የገቢ አቅምን ማሳደግ የከተሞችን ገጽታ መለወጥ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የመሰረተ 

ልማት ስራን ለማስፋፋት፣የአርሶ አደሩን ህይወት ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ 

ለማድረግ አመራሩ ፣ፈጻሚ አካላት ፣ የንግዱ ማህበረሰብ እና መላው የክልሉ ህዝብ 

የድርሻውን እንዲወጣም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል። 

በሌላ በኩል የንግድ ስርዓቱን ለማዘመን የተሳለጠ አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ ስለመሆኑም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

በንግድ ስርዓቱ ውስጥ ህገ-ወጥነትን መከላከል፣ የግብይት ማዕከላትን የማስፋፋት፣ምርትን 

በበቂ ሁኔታ ማቅረብ፣የዋጋ ንረትን መቆጣጠር፣የሸማች ማህበራትን ማጠናከር እንዲሁም 

ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመግባባት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት 

ሰጥተዋል። 

በመድረኩ በሁለቱም ሴክተሮች ወቅታዊና አስፈላጊ አጀንዳዎች ላይ በቂ ምክክር በማድረግ 

በተግባር የሚተረጎሙ አቅጣጫቻዎችን ማስቀመጥ የሚያስችል ስለመሆኑም ርዕሰ 

መስተዳድሩ አመላክተዋል።

Read more
በክልሉ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ 1 ነጥብ 87 ቢልዮን ሀብት መሰብሰብ ተችሏል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

በክልሉ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ 1 ነጥብ 87 ቢልዮን ሀብት መሰብሰብ 

ተችሏል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

ሆሳዕና፣ነሐሴ 1/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 

6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ 

ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )ለምክርቤቱ 

ትላንት ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት በክልሉ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ 1 ነጥብ 

87 ቢልዮን ሀብት መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል። 

በዚህም አዲስ የቅድመ-አንደኛ 72 አንደኛና መካከለኛ 30፣ ሁለተኛ ደረጃ 5 ትምህርት

ቤቶች መገንባታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አብራርተዋል። 

በሁሉም እርከን የአዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣የነባር ክፍሎች ጥገና፣ ሌሎች 

የትምህርት ግብአቶችን ለማሟላት ጥረት መደረጉን አስረድተዋል። 

በክልሉ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያጋጠመውን ስብራት መጠገን የሚያስችሉ ዕቅዶች 

ተዘጋጅተው በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በዘርፉ በተደረገ ሁሉን አቀፍ ጥረት የተማሪዎች ሥነ-ምግባርና ውጤት እንዲሁም 

በትምህርት ጥራት ላይ መሻሻል ታይቷል ብለዋል፡፡ 

በክረምት ወቅት የተማሪዎችን ውጤትን ለማሻሻል በመምህራንና በበጎ ፈቃደኛ 

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አማካይነት ለ294 ሺ 284 ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት 

ተስጥቷል፡፡ 

በበጀት ዓመቱ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ህብረተሰቡ በገንዘብ፣ በአይነት፣ በጉልበት 

እና በዕውቀት የላቀ ተሳትፎ ስለማድረጉም ጠቁመዋል።

Read more
ያለፉት ሶስት ዓመታት ጉዞ ድልም ፈተናም ነበረው:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

ያለፉት ሶስት ዓመታት ጉዞ ድልም ፈተናም ነበረው:- ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች 

ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ 

ከተማ እየተካሔደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

እንደገለጹት እያንዳንዱ ስራ ላይ ከ10 እስከ 15 በመቶ በመጨመር እቅድ 

ተዘጋጅቷል ብለዋል። 

የክልሉን የመልማት አቅም በጥናት መለየት ተችሏል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 

ይህም የምርታማነት መጠን ለማሳደግ እንደሚረዳ አስረድተዋል። 

የበጀት ዓመቱን የዝግጅት ምዕራፍ አስቀድሞ ተግባራዊ ማድረግ ስለመቻሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። 

አዳዲስ ሀሳቦችን በማፍለቅ ለተሻለ ለውጥ የሚተጋ አመራር እና ፈጻሚ መፍጠር 

ስለመቻሉም ጠቅሰዋል። 

ያለፉት ሶስት ዓመታት ጉዞ ፈተናም ድልም ነበረው:- ፈተናዎችን ወደ ድል የመቀየር 

ስትራቴጂ ተቀርጿል ብለዋል። 

በክልሉ መሰረታዊ የሆኑ ችግሮችን መፍታት ተችሏል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ስራን 

መሰረት ያደረገ የአመራር ስርዓት ተፈጥሯል። 

የክልሉ መንግስት የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች 

ላይ ትኩረት ማድረጉን ጠቅሰዋል። 

የትምህርት ስራ በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ እንደሚሄድ ርዕሰ መስተዳድሩ በማብራሪያቸው 

ገልጸዋል። 

በመምህራን፣በትምህርት አመራር፣በግብአት አቅርቦት እንዲሁም በስርዓተ ትምህርት 

ላይ በትኩረት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

ባለፉት ሁለት ዓመታት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገር የሚያስችል አቅም መፍጠር 

ተችሏል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

ከመኖሪያ ቤት ቦታ አቅርቦት ጋር በተያያዘ በሆሳዕና ከተማ ለ285 ማህበራት በተቀመጠው 

ቅደም ተከተል መሰረት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል። 

በክልሉ በተለያዩ ከተሞች ከ200 ኪ/ሜ በላይ የኮሪደር ልማት ስራ ተግባራዊ እየተደረገ 

ስለመሆኑም ጠቅሰዋል። 

የጠራ አስተሳሰብ እና ተግባር ባለባቸው ዘርፎች ውጤት ተመዝግቧል ያሉት ርዕሰ 

መስተዳድሩ በተቃራኒው ደግሞ ዝቅተኛ አፈጻጸም ተመዝግቧል። 

በብልጽግና እሳቤ ውስጥ ሆኖ ተግባርን መምራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ ተግባቦት 

ስለመፈጠሩም ጠቅሰዋል። 

ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን አብራርተዋል። 

የምክር ቤት አባላት በጋራ ትርክት ግንባታ ላይ ሚናቸውን እንዲወጡም ርዕሰ መስተዳድሩ 

ጥሪ አቅርበዋል። 

የጋራ ትርክት ለሀገረ መንግስት እና ለተቋም ግንባታ የሚኖረው አበርክቶ የላቀ ስለመሆኑም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። 

የኑሮ ማረጋጋት እና የስራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 

ከሰንበት እስከ ሰንበት እና የምርት አቅርቦት ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል። 

የከተሞችን እድገት ለማፋጠን የገቢ መሰረትን ማስፋት እና ኢከኮሚው የሚያመነጨውን ገቢ 

መሰብሰብ ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል። 

የክልሉን ከተሞች ተወዳዳሪ እና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የጋራ ጥረት እንደሚጠይቅም 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

Read more
በበጀት አመቱ ከ619ሺ በላይ ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

በበጀት አመቱ ከ619ሺ በላይ ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ 

ማድረግ ተችሏል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች 

ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ 

ከተማ እየተካሔደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

እንደገለጹት በክልሉ በመንግስት፣በረጂ እና በአጋር አካላት ድጋፍ በገጠር እና 

በከተሞች 207 የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ተችሏል። 

ይህን ተከትሎም በበጀት ዓመቱ ከ619ሺ በላይ ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ 

ተጠቃሚ ማድረግ ስለመቻሉም አመላክተዋል። 

የመስኖ አውታር ግንባታን በሚመለከት 610 ሄ/ር የሚያለሙና 2ሺ 300 አባዎራና 

እማዎራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የ5 ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ አገልግሎት 

መስጠት መጀመራቸውን ጠቁመዋል።
በበጀት ዓመቱ ለ792 የማዕድን ማምረቻ ይዞታዎች ላይ ለባህላዊ እና ለአነስተኛ ደረጃ 

ኮንስትራክሽን የማምረት የስራ ፈቃድ መሰጠቱን ተናግረዋል። 

በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ስርጭት፣

አዳዲስ የቤተሰብ ባዮ ጋዝ ግንባታ፣የሶላር ማሾዎች ስርጭት እና መሰል ተዛማጅ 

ስራዎች ተግባራዊ መደረጉን አብራርተዋል።

Read more
በበጀት አመቱ 21 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ የኢንቨስትመንት ልማት ፕሮጀክቶች ፍቃድ ወስደዋል :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

በበጀት አመቱ 21 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 

የኢንቨስትመንት ልማት ፕሮጀክቶች ፍቃድ ወስደዋል :-

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ 

ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ 

መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው 

(ዶ/ር እንደገለጹት በበጀት አመቱ ፈቃድ የወሰዱ የኢንቨስትመንት 

ፕሮጀክቶች 21 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ካፒታል አስመዝግበዋል 

ብለዋል። 

ከክልል ምስረታ በኋላ በግብርና 145 በኢንዱስትሪ 103 እና 

በአገልግሎት 78 በድምሩ ከፀደቁ 326 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 

ውስጥ 271 ያህሉ ከሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ መሬት 

ተረክበዋል።የተቀሩት ደግሞ በሃደት ላይ እንደሆኑ ርዕሰ መስተዳድሩ 

አብራርተዋል።

በክልሉ በግብርና ፣በአገልግሎት እና በኢንዱስትሪ 1ሺ555 ፕሮጀክቶችን 

መከታተል ስለመቻሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አብራርተዋል። 

በክልሉ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብድር በማቅረብ 

የማሽነሪ ሊዝ አቅርቦት ማመቻቸት ስለመቻሉም ጠቁመዋል። 

በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ መነቃቃት በመፍጠር ረገድ የተጀመረው ኢትዮጵያ 

ታምርት ንቅናቄ መድረክም ከክልል ጀምሮ በየደረጃው እንዲካሄድ ተደርጓል ሲሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አብራርተዋል። 

ምክር ቤቱ በከሰዓት ዉሎው በ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት የጀመረው ውይይት 

ቀጥሏል።

Read more
በክልሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት ውጤታማ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

በክልሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነትን 

ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት ውጤታማ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች 

ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ 

ከተማ እየተካሔደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት 

ጊዜ እንደገለጹ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነትን 

ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት ውጤታማ ነው ብለዋል። 

በሁሉም የምርት ወቅቶች 1ሚሊየን 259ሺ 472 ሄ/ር መሬት በማልማት

ከ160 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ተገኝቷል ብለዋል። 

በመኸር እርሻ በአዝርዕትና በሆርቲካልቸር ከ57ሚሊየን 547ሺ ኩንታል 

በላይ ምርት መገኘቱን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቁመዋል። 

በክልሉ በበልግ የአዝመራ ወቅት 267ሺ 817 ሄ/ር ማሳ በማልማት ከ12 ነጥብ 

5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ስመገኘቱም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

በአዝርዕትና በሆርቲካልቸር ስብሎች 437ሺ 182 ሄ/ር ማሳ በማልማት ከ 62 

ሚሊየን ,872 ሺ ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ ተችሏል ሲሉም ርዕሰ 

መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል። 

በክልሉ በአትክልት በቅባትና በስራስር ሰብሎች የላቀ ውጤት መመዝገቡን 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በምርት ዘመኑ በኩታ ገጠም እርሻ ከ6ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት 

መሰብሰብ መቻሉንም ጠቅሰዋል። 

በፀደይ ወቅት እርሻ 63ሺ540 ሄክታር መሬት በማልማት ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን 

በላይ ኩንታል ምርት ተሰብስቧል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው 

ጠቅሰዋል።

በክልሉ በበጋ መስኖ ልማት ከ37 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ስለመገኘቱም 

አብራርተዋል።

Read more
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 

5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ።

ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ 

ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ 

መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው።

ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ቆይታው የክልሉን መንግሥት አስፈፃሚ 

መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2019 

በጀት ዓመት የእቅድ እቅጣጫዎች ላይ ይመክራል። 

በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በኦዲት ቢሮ እና በምክር ቤት ጽ/ቤት 

ያሳለፍነው በጀት አመት አፈጸምና በያዝነው በጀት አመት ጠቋሚ 

እቅዶች ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። 

በጉባኤው የክልሉ የ2019 አጠቃላይ በጀት እንደሚታወጅ ይጠበቃል።

Read more
በክልሉ በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን የላቀ ውጤት ቀጣይነት ማረጋገጥ ይገባል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በክልሉ በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን የላቀ ውጤት ቀጣይነት 

ማረጋገጥ ይገባል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 28/2018የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ እና በቀቤና ልዩ ወረዳ 

በኩታ ገጠም እየለማ ያለ የበቆሎ ማሳ ተመልክተዋል 

ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ ምልከታቸው እንደገለጹት በክልሉ በግብርናው 

ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን የላቀ ውጤት ቀጣይነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል። 

በቀቤና ልዩ ወረዳ ፍቃዱ ቀበሌ ከ16ሺ ሄ/ር በላይ ማሳ በበቆሎ ክላስተር 

እየለማ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

በአበሽጌ ወረዳ ደግሞ 39ሺ ሄ/ር ማሳ በበቆሎ ክላስተር መልማቱንም ርዕሰ 

መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በሁለቱ አጎራባች ወረዳዎች የግብርና ልማት ስራው በተጠናከረ መልኩ እየለማ 

ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

በጋራ ሆኖ መስራት ውጤታማ እንደሚያደርግ ከሁለቱ አካባቢዎች ተገንዝበናል 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የግብርና ግብአት አጠቃቀም እና መካናይዜሽንን ማስፋፋት 

ለምርታማነት ማደግ ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል። 

በቀቤና ልዩ ወረዳ ፍቃዱ ቀበሌ በቆሎ በሄክታር ከ90 እስከ 110 ኩንታል እየተመረተ 

መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል። 

በተመሳሳይ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ደግሞ በቆሎ በሄክታር ከ90 እስከ 120 ኩንታል 

ማምረት እንደሚቻል አመላክተዋል። 

በሁለቱ አካባቢዎች የተገኘው የምርታማነት እድገት እንደ ክልልም ሆነ እንደ ሀገር ልምድ 

ይወሰድበታል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

አርሶ አደሮች ከግብርና ባለሙያዎች የሚሰጣቸውን ሙያዊ ድጋፍ በመጠቀም እና 

በትብብር መስራት በመቻላቸው በዘርፉ የላቀ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ርዕሰ 

መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

በክልሉ ቅድመ በልግ እና ጸደይን በመጨመር አምስት የአዝመራ ወቅቶችን መጠቀም 

በመቻሉ የምርታማነት መጠን እያደገ መሆኑን በአብነት ጠቅሰዋል። 

በክልሉ የግብርናው ዘርፍ ሀብት የመፍጠር እና ወደ መካናይዜሽን የመሻገር አቅም

እየጨመረ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

የአርሶ አደሮችን ኑሮ ለመቀየር የገጠር ኮሪደር ማስፋፋት አስፈላጊ ስለመሆኑም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። 

በተያዘው የምርት ዘመን የዝናብ እጥረት ማጋጠሙን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ 

ልዩ ልዩ ጫናዎችን በመቋቋም በግብርና ልማት ስራቸው ለውጥ ለማምጣት እየተጉ 

ላሉ አርሶ አደሮች ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።

Read more
በክልሉ በአንድ ጀንበር ከ10 ሚሊየን በላይ ችግኞች የመትከል ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በክልሉ በአንድ ጀንበር ከ10 ሚሊየን በላይ ችግኞች የመትከል ዘመቻ 

ተጠናክሮ ቀጥሏል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 27/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በቀቤና ልዩ ወረዳ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን 

የችግኝ የተከላ መርሐ-ግብር ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

እንደገለጹት በሀገር አቀፍ ደረጃ 800ሚሊየን ችግኞች በአንድ ጀንበር 

ይተከላል ብለዋል። 

በክልሉ ከ10 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል ወደ ተግባር መገባቱን ርዕሰ 

መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

መላው የክልሉ ህዝብ በዛሬው እለት በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ እያካሄደ 

መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በሀገር አቀፍ ደረጃ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ተቀምጦለት በክቡር ጠቅላይ 

ሚኒስትሩ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት ባለፉት ሰባት አመታት የአረንጓዴ አሻራ 

ፕሮግራም ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን አብራርተዋል። 

በአለም አቀፍ ደረጃ ኢተገማች የአየር ንብረት ለውጥ እየተከሰተ ስለመሆኑ 

የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ሊያጋጥሙን የነበሩ አደጋዎችን እየተከላከልን 

ነው ብለዋል። 

የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ህብረትን፣መደጋገፍን እና ሌሎች መልካም 

እሴቶቻችንን የሚያንጸባርቅ መሆኑን ጠቅሰዋል። 

አረንጓዴ አሻራ የጋራ ትርከክት መገንቢያ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 

በዚህም ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ያስተሳሰረ ነው ብለዋል። 

በክልሉ በእምነት ተቋማት፣በትምህርት ቤቶች፣በመንገድ አካፋዮች፣

በመዝናኛ ስፍራዎች እና በሌሎችም ተቋማት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም 

እየተካሄደ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

የሚተከሉት ችግኞች ለምግብነት፣ለኢንዱስትሪ ግብአት እና ለስነ ውበት 

አገልግሎት ጠቀሜታ እንዳላቸውም አብራርተዋል።

Read more