![]() |
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር ) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የባንኩ የሆሳዕና ዲስትሪክት አመራሮች ጋር ተወያዩ ፤ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር ) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የባንኩ የሆሳዕና ዲስትሪክት አመራሮች ጋር ተወያዩ ፤ ሆሳዕና ፣ ጥር 16 ፣ 2017፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር ) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንትና የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሀላፊ እና ከሆሳዕና ዲስትሪክት አመራሮች ጋር ባንኩ የክልሉን የልማት ሥራዎችን ይበልጥ መደገፍ በሚችልባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸዉ ምክክር አድርገዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንትና የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሀላፊ አቶ ሙሉነህ ለማ ፣ የባንኩ የሆሳዕና ዲስትርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ምስጋና ለጌታ ግርማ ፣ በሆሳዕና ዲስትሪክት የነጋዴ ደንበኞችና የከፍተኛ ደንበኞች ሀላፊ አቶ ጌታሁን ሽጉጤ በምከክር መድረኩ የተገኙ ሲሆን፣ የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪዎች ቡድንም በመድረኩ ተገኝቷል። |
![]() |
መስተዳድር ምክር ቤቱ በከሰዓት ቆይታዉ የክልሉን መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ አመት አፈጻጸም እየገመገመ ዉሏል፤ መስተዳድር ምክር ቤቱ በከሰዓት ቆይታዉ የክልሉን መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ አመት አፈጻጸም እየገመገመ ዉሏል፤ ሆሳዕና፣ ጥር 15፣ 2017፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በከሰዓት ቆይታዉ የክልሉን መንግስት የ6 ወራት አፈጻጸም አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት ላይ እየመከረ ዉሏል። መስተዳድር ምክር ቤቱ በ22ኛ መደበኛ ስብሰባው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ የሚያደርገው የምክክር መድረክ በነገው እለትም የሚቀጥል ይሆናል። |
![]() |
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ ሆሳዕና፣ ጥር 15፣ 2017፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር በ22ኛ መደበኛ ስብሰባው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየመከረ ይገኛል ። መስተዳድር ምክር ቤቱ የክልሉን መንግስት በ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ በስፋት እንደሚመክር ተመላክቷል። |
![]() |
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በመስቃን እና ማረቆ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋገሩ፣ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በመስቃን እና ማረቆ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋገሩ፣ ሆሳዕና፣ጥር 14፣ 2017 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ከዚህ ቀደም በመስቃን እና ማረቆ አዋሳኝ ቀበሌያት በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋገሩ። ርዕሰ መስተዳድሩ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ እና በማረቆ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌዎች በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት የክልሉ መንግስት ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል። |
![]() |
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የግብርና ኤግዚቢሽን እና ባዛር መርቀው ከፈቱ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የግብርና ኤግዚቢሽን እና ባዛር መርቀው ከፈቱ ሆሳዕና፣ጥር 14፣2017፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ግብርና ቢሮ የተዘጋጀውን የግብርና ኤግዚቢሽን እና ባዛር በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ መርቀው ከፍተዋል። በኤግዚቢሽን እና ባዛሩ የክልሉን የመልማት አቅም እና የግብርናውን ዘርፍ ውጤታማነት መለየት እንደሚያስችልም ተመላክቷል። |