በበጀት አመቱ 21 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ
የኢንቨስትመንት ልማት ፕሮጀክቶች ፍቃድ ወስደዋል :-
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ
ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ
መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው
(ዶ/ር እንደገለጹት በበጀት አመቱ ፈቃድ የወሰዱ የኢንቨስትመንት
ፕሮጀክቶች 21 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ካፒታል አስመዝግበዋል
ብለዋል።
ከክልል ምስረታ በኋላ በግብርና 145 በኢንዱስትሪ 103 እና
በአገልግሎት 78 በድምሩ ከፀደቁ 326 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች
ውስጥ 271 ያህሉ ከሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ መሬት
ተረክበዋል።የተቀሩት ደግሞ በሃደት ላይ እንደሆኑ ርዕሰ መስተዳድሩ
አብራርተዋል።
በክልሉ በግብርና ፣በአገልግሎት እና በኢንዱስትሪ 1ሺ555 ፕሮጀክቶችን
መከታተል ስለመቻሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አብራርተዋል።
በክልሉ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብድር በማቅረብ
የማሽነሪ ሊዝ አቅርቦት ማመቻቸት ስለመቻሉም ጠቁመዋል።
በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ መነቃቃት በመፍጠር ረገድ የተጀመረው ኢትዮጵያ
ታምርት ንቅናቄ መድረክም ከክልል ጀምሮ በየደረጃው እንዲካሄድ ተደርጓል ሲሉም
ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አብራርተዋል።
ምክር ቤቱ በከሰዓት ዉሎው በ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት የጀመረው ውይይት
ቀጥሏል።