የአማካሪዎች ጽ/ቤት
![]() | |
![]() | ![]() |
የአማካሪዎች ጽ/ቤትዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
- የአስፈጻሚ ተቋማት ዕቅድ፣ ከአጠቃላዩ ፖሊሲ ግቦችና ከክልሉ ስትራቴጂክ ዕቅድ ጋር የሚጣጣም መሆኑን የመገምገምና የማረጋገጥ ስራዎችን ይሰራል፣
- የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና መሰረተ-ልማት ሴክተሮችን የዕቅድ አፈጻጸም ይከታተላል፣ ይደግፋል በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ግብረ መልስ እንዲሰጥባቸው ያደርጋል፣
- አፋጣኝ ምላሽ የሚያስፈልጋቸዉን አኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና የመሰረተ-ልማት ጉዳዮችን በማጣራት ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
- በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ መሰረተ-ልማት ጉዳዮች በወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አፈፃፀም ዙሪያ የጥናት ስራ መስራት፣
- ከአስፈፃሚ ተቋማት የአፈፃፀም ሪፖርቶችን የማሰባሰብ፣ የማጣራትና የማጠናቀር ስራ ማከናወን፣
- በየደረጃዉየሚገኙ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና መሰረተ ልማት አማካሪዎችን መዋቅር ይከታተላል ይደግፋል፣
- በየደረጃዉ የሚገኙ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና መሰረተ ልማት መዋቅሮች ላይ የሚሰሩ ፈፃሚዎችን አቅም የማሳደግ ስራዎችን ይሰራል፣
- ሥርዓተ-ምግብ ተኮር ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞች እና መመሪያዎች በምግብና ሥርዓተ-ምግብ ተግባሪ ሴክተሮች እንዲተገበር ማስተባበር፣ ትግበራውን የመከታተልና የመገምገም ስራ፣
- ወረዳን መሰረት ያደረገ ሥርዓተ-ምግብ ተኮር ዝርዝር እቅድ እንዲዘጋጅ እና እንዲተገበር ድጋፍና ክትትል የማድረግና የመገምገም ስራ፣
- በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተቀናጀ የሥርዓተ-ምግብ መረጃ ሥርዓት እንዲጠናከር፣ ጠቋሚዎች እንዲለዩ፣ እንዲካተቱና እንዲተገበሩ ተግባሪ ሴክተሮችን የማስተባበር ስራ፣
- ሥርዓተ-ምግብ ተኮር ተግባራት በሴክተሮች ሰነዶች ተካተው መተግበራቸውን የማረጋገጥ፣
- ምርጥ ተሞክሮዎችን መለየት፣ መቀመርና የማስፋት ስራ መስራት፣
- የሕግ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና መሰረተ ልማት ጉዳዮች በመለየት ሕግ እንዲወጣላቸው አስተያየት ማቅረብ፣
- የፕሮጀክቶች ፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ያካሂዳል