የጽ/ቤቱ አጠቃላይ ገጽታ(ዳራ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የአስተዳደር ሴክተር በ 2015 ዓ.ም በተሻሻለው የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 70 እና 72 ለመስተዳድር ምክር ቤቱና ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችለው ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ አደረጃጀትና አሰራሮችን በመዘርጋት የክልሉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ለማፋጠን እና ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ብሎም የተገልጋዩን ህብረተሰብ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል፡፡
የርዕሰ መስተዳድርና መስተዳድር ምክር ቤት ጽ/ቤት፣ የአማካሪዎች ጽ/ቤት፣ የህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት፣ የህዝብ ግኑኝነትና ማህበረሰብ ንቅናቄ ዘርፍ፣ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ እንዲሁም የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት በማጠናቀቅ አራት ተልዕኮ ተኮር ዳይሬክቶሬቶች እና ሌሎች የድጋፍ ሰጭ ዳይሬክቶሬቶች ጽ/ቤቱ በአዋጅ የተሰጡትን ተልዕኮዎች ለመወጣት በሚያስችለው አግባብ ተደራጅተዋል፡፡
በጽ/ቤቱ የተደራጁ የሥራ ክፍሎች ሌሎች የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍና በማስባበር የክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ እና የመስተዳድር ምክር ቤቱ የዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የክልሉ ህዝብ የልማት፣ የሠላም፣ የመልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በተሟላ መልኩ ምላሽ እንዲያገኙ እና ህብረተሰቡ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡