የርዕሰ መስተዳድርና መስተዳድር ምክር ቤት ጽ/ቤት
![]() | ||
![]() | ![]() | ![]() |
![]() |
የርዕሰ መስተዳድርና መስተዳድር ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
- የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የሰው ሀይል እና ሎጅስቲክስ እንዲሟላ ያደርጋል፣
- የመስተዳድር ምክር ቤቱን የስብሰባ ሂደቶች በመቅረፀ-ምስል፣ መቅረፀ-ድምፅና በህትመት ሠነዶችን በአግባቡ በመያዝና በመጠበቅ ለሚፈቀድላቸዉ አካላት የማቅረብ ስራ ይሰራል፣
- የመስተዳድር ምክር ቤቱን ቃለ-ጉባዔ መያዝ እና የሚተላለፉ ዉሳኔዎች ምስጢራዊነታቸዉ ተጠብቆ ለሚመለከተዉ አካል ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
- ለካቢኔ የሚቀርቡ ጉዳዮች በመስተዳድር ምክር ቤት አሰራር ደንብ መሰረት ተገቢውን የጥራት ደረጃ ጠብቀው መቅረባቸውን ያረጋግጣል፡፡
- የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የሚያፀድቃቸዉን ደንቦችና መመሪያዎች አሳትሞ ለሚመከታቸው አካላት እንዲሰራቹ ያደርጋል፣
- ከመንግስት መ/ቤቶች ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ለውይይት የሚቀርቡ ሰነዶችና የውሳኔ ሀሳቦችን በተመለከተ የማማከር፣ ድጋፍ የመስጠትና የማስተባበር ስራ ይሰራል፣
- በመስተዳድር ም/ቤቱ ለሚቋቋሙ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ድጋፍ የመስጠትና የማስተባበር ስራ ይሰራል፣
- በዞኖች፣ በልዩ ወረዳዎችና ወረዳዎች የካቢኔ የአሰራር ስርዓት ደንቡን የተከተለ ስለመሆኑ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣
- ከዞን እና ልዩ ወረዳዎች የሚቀርቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን ተገቢነት በማጣራት፣ ፕሮጀክቶቹ እንዲገመገሙ በማድረግ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በማቅረብ ያስወስናል፤ ውሳኔዎቹንም ለዞኖችና ለልዩ ወረዳዎች በደብዳቤ ያሳውቃል፤
- ከዞን እና ልዩ ወረዳዎች የሚቀርቡ የምትክ መሬት ጥያቄዎችን ተገቢነት በማጣራት፣ ጥያቄዎቹ በክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ እንዲገመገሙ በማድረግ በሚቀርበው የአስተያየትና የውሳኔ ሀሳብ መነሻ ውሳኔዎቹን ለዞኖችና ለልዩ ወረዳዎች በደብዳቤ ያሳውቃል፤
- በክልሉ ከሚገኙ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት፣ ከዞንና ልዩ ወረዳ መዋቅሮች እንዲሁም ከግለሰቦች የሚቀርቡ የድጋፍ፣ የትብብር፣ የምደባ እና ሌሎች ጥያቄዎችን ተቀብሎ በመመርመር ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
- ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ሀገር ወደ ክልሉ ለሚመጡ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮችና የአለምአቀፍ ድርጅቶች ተጠሪዎች የፕሮቶኮል ሽፋን የመስጠት አገልግሎት፣