የህግ እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ጽ/ቤት

የህግ እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ጽ/ቤት
- የሪፎርም ኘሮግራሞች ጉዳዮችን አተገባበርን ይከታተላል፣ ይደግፋል ግብረ መልስ እንዲሰጥባቸው ያደርጋል፣
- የመልካም አስተዳደር ፖኬጆች አተገባበርና ዉጤታማነትን በተመለከተ የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ያከናውናል፣
- በየደረጃው የተዋቀሩ የፀጥታ ምክር ቤቶች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በሚወጡበት አግባብ የመደገፍና የመከታተል ስራ ይሰራል፣
- የፀጥታ ሴክተሩ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ በሚችለበት አግባብ አፈፃፀሙን የመከታተልና የመደገፍ ስራ ይሰራል፣
- በአጎራባች ክልሎች ድንበር አካባቢዎች የሠላምና የልማት ስራዎች በቅንጅት እንዲከናወኑ ይደግፋል፣
- ወቅታዊ አጠቃላይ የፀጥታ ሪፖርቶችን በመቀበል፣ በመተንተንና ዕንድምታዎችን ለይቶ ሪፖርት የማቅረብና ግብረ መልስ እንዲሰጥባቸው ያደርጋል፣
- አስተዳደራዊ ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን ይቀበላል፣ ያጣራል ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
- የቅሬታናአቤቱታ መንስኤዎች ላይ ጥናት በማካሄድ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ይሰራል፣
- በየደረጃዉየሚገኙ የቅሬታና አቤቱታ መዋቅሮችን ይከታተላል ይደግፋል፣
- በየደረጃዉ የሚገኙ የቅሬታና አቤቱታ መዋቅሮች ላይ የሚሰሩ ፈፃሚዎችን አቅም የማሳደግ ስራዎችን ይሰራል፣
- የህግ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲያገኙ ያቀረቡትን ጥያቄ ተገቢነት በማጣራት ለክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አቅርቦ ይቅርታ እንዲያገኙ ይሰራል፣
- የሰብአዊ መብቶች አያያዝና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንዲሻሻል የሚያስችል አሰራር እንዲኖር ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት ይሰራል፣
- በተቋማትና በክልሉ ፍትህ ቢሮ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ ረቂቅ ህጎችን የመመርመር እና ለመስተዳድር ምክር ቤቱ ማብራሪያ የማቅረብ ስራ ይሰራል፣
- የሌሎች ተቋማትን ረቂቅ ህጎች መሰረታዊ የህግ መርሆዎችን የተከተሉ መሆናቸዉንና አስፈላጊነታቸዉን አጣርቶ አስተያየትና የህግ ምክር ይሰጣል፣
- በህግ ጉዳዮች ላይ ለመስተዳድር ም/ቤቱም ሆነ ለርዕሰ-መስተዳድሩ ተገቢውን ሙያዊ አስተያየትና የመፍትሄ አማራጮችን የማቅረብ ስራ ይሰራል፣
- የፍትህ ስርአት ማሻሻያ ፕሮግራም በሚመለከታቸው ተቋማት ተቀናጅቶ ሊተገበር በሚችልበት ሁኔታ መታቀዱንና መከናወኑን በመከታተል ለርዕሰ መስተዳድሩ ሪፖርት በማቅረብ ግብረ መልስ እንዲሰጥበት ያደርጋል፣
- በክልሉ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ዙሪያ በተለያዩ ተቋማት የሚከናወኑ ተግባራትን የመከታተልና የመደገፍ ስራ ይሰራል፣
- ምርጥ ተሞክሮዎችን መለየት፣ መቀመርና የማስፋት ስራ መስራት፡፡