Skip to main content
በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት ያጋጠሙ ፈተናዎችን በሰከነ እና በበሳል የአመራር ጥበብ በመሻገር ወደ ድል መቀየር ተችሏል :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻውጣሰው (ዶር)

በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት ያጋጠሙ ፈተናዎችን በሰከነ እና በበሳል 

የአመራር ጥበብ በመሻገር ወደ ድል መቀየር ተችሏል :- ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻውጣሰው (ዶር) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 22/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 በጀት 

ዓመት የፓርቲ  እና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም እና በ2019 በጀት 

አመት ዕቅድ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ክልል አቀፍ የከፍተኛ 

አመራሮች መድረክ እየተካሔደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶር) 

በምክክር መድረኩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት የባለፉት 

3 ዓመታት ጉዞ በበርካታ ድሎች እና ፈተናዎች የታጀበ ነበር ብለዋል። 

በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት ያጋጠሙ ፈተናዎችን በሰከነ እና በበሳል 

የአመራር ጥበብ በመሻገር ወደ ድል መቀየር ተችሏል መቻሉን ርዕሰ 

መስተዳድሩ አስረድተዋል። 

ክልሉ ሲመሰረት የተደበላለቁ አመለካከቶች፣የእዳ ጫና ፣የሀብት እጥረት፣

የሀሰተኛ ሚዲያዎች መበራከት፣ደመወዝ በአግባቡ መክፈል ያለመቻ እና 

ሌሎች በርካታ ተግዳሮቶች ማጋጠማቸውን ርዕሰ መስተዳደሩ አብራርተዋል። 

ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በውስጥ አቅም በመፍታ ለተጨማሪ ድሎች በትኩረት 

እየተሰራ ነው ብለዋል። 

አዲስ ክልል ብንሆንም አጭሩንም ረጅሙንም ሩጫ ለማጠናቀቅ በቂ ስልት 

በመንደፍ ክልሉን የብልጽግና ተምሳሌት፣የተሞክሮ ማዕከል፣ የተረጋጋና 

ሰላማዊ ክልል መፍጠር መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው 

አመላክተዋል።

ክልሉ የህብረ ብሔራዊነት ተምሳሌት እንዲሆን በተሟላ መንገጥ ወደ ተግባር 

መገባቱን ምርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

በክልሉ በሁሉም መስክ በርካታ ስኬታማ ስራዎች መኖራቸውን መገንዘብ 

ተችሏልያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በ2018 በጀት ዓመት መደበኛ የመንግስት፣

የፓርቲ እንዲሁም የምርጫ ስራን በስኬት መፈጸም ስለመቻሉም ርዕሰ 

መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል። 

የተለያዩ ደባል አጀንዳዎች በመኖራቸው ባሰብነው ፍጥነት መሰረት መጓዝ 

እንዳንችል አድርጎናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ የነጠላ ትርክት መበራከት፣

በመዋቅሮች እና በሴክተሮች የአፈጻጸም ልዩነት መኖር እንዲሁም የስልጣን አተያይ 

ችግሮችን ጠቁመዋል። 

ያጋጠሙ ችግሮችን በአግባቡ በመገምገም ማስተካከል እንደሚገባም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። 

በክልሉ በመንግስት እና በፓርቲ ስራዎች ጥንካሬዎችን ማስቀጠል እና በአፈጻጸም

ረገድ የተስተዋሉ ውስንነቶችን ማረም የሚያስችል መድረክ ነው ያሉት ርዕሰ 

መስተዳድሩ ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ የጋራ ተግባቦት ይፈጠራል ብለዋል። 

በመድረኩ የ2018 በጀት አመት ማጠቃለያ ፣ የባለፉት 3 አመታት ጉዞ እና የባለፉት 

አምስት ዓመታት የምርጫ ዘመን ማጠቃለያ ሀሳቦች ላይ ምክክር እንደሚደረግም 
ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት በጽህፈት ቤታቸው እየገመገሙ ነው

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ባለፉት ሁለት 

ዓመታት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት 

አፈጻጸም ሪፖርት በጽህፈት ቤታቸው እየገመገሙ ነው 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 18/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከተረጂነት ወደ 

ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት 

በጽ/ቤታቸው እየገመገሙ ነው 

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ብሎም 

ከተረጂነት ለመሸጋገር ባለፉት ሁለት ዓመታት በሰባት መዋቅሮች በ35 ወረዳዎች 

ልዩ ልዩ ስራዎች ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል። 

በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የተገኘውን ሀብት መነሻ በማድረግ በወረዳዎች 

እቅድ ተዘጋጅቶ ስራው ሲመራ መቆየቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በተከናወኑ ተግባራት ክልሉ ሰብአዊ 

ድጋፍ በራስ አቅም መሸፈን የሚያስችለውን ስርዓት መዘርጋት ስለመቻሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

ከጥቅምት 30/2019 ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተረጂነት ለመውጣት ዝግጅት 

እየተደረገ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል። 

ይህን ተከትሎም በክልሉ የሰብአዊ ድጋፍ ሉአላዊነት ለማስጠበቅ የተሟላ ዝግጅት 

በማድረግ የጋራ ተግባቦት መፍጠር የሚያስችል መድረክ ስለመሆኑም አስረድተዋል። 

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ማዕረጉ ማቲዎስ በክልሉ ባለፉት 

ሁለት ዓመታት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም 

ሪፖርት እያቀረቡ ነው።

Read more
ጂኮ ፓርክ ክልሉን ከማስተዋወቅ ባለፈ ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው የሚገኘውን ሀብት ያሳድጋል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ጂኮ ፓርክ ክልሉን ከማስተዋወቅ ባለፈ ከቱሪዝም 

ኢንዱስትሪው የሚገኘውን ሀብት ያሳድጋል:-

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በተገኙበት የማዕከላዊ

ኢትዮጵያ ክልል ስምጥ ሸለቆ ጂኦ ፓርክን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ 

በተከናወኑ ተግባራት ላይ ያተኮረ ምክክር እየተካሔደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የክልሉ መንግስት በሁሉም መስክ የላቀ የህዝብ 

ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረጉ ስራዎች ላይ በትኩረት 

እየተሰራ ነው ብለዋል። 

ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ 

እየተካሔደ ያለው ጥረት ስኬታማ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ 

ጠቁመዋል። 

የልማት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የማጠናቀቅ አብነት የሆነ ክልል ነው ያሉት 

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል። 

በመድረኩ የቀረበው ሪፖርት እንደሚያመላክተው የጂኮ ፓርኩ እውን 

መሆን ክልሉን እና ሀገሪቱን በማስተዋወቅ ረገድ የጎላ ድርሻ ይኖረዋል። 

የጎብኚዎችን ፍሰት በመጨመር የቱሪዝም ዘርፉን ከማነቃቃት ባለፈ 

የኢኮኖሚ አቅምን ያሳድጋል። 

ለሆቴል ኢንዱስትሪ ማደግ የሚኖረው አበርክቶ የላቀ ሲሆን ለተለያዩ 

ለምርምር እና ለጥናት ስራዎች ማዕከል በመሆን እንደሚያገለግልም 

ተመላክቷል። 

ጂኦ ፓርኩ አለም አቀፍ እውቅና ስለሚኖረው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች እና 

ኢኒሼቲቮች መነሻ ስለመሆኑም በሪፖርቱ ተመላክቷል። 

የባህል እሴቶቻችን ይበልጥ ከማስተዋወቅ ባለፈ ለህብረተሰቡ የተቀናጀ 

የኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ እንደሚያስችልም ተጠቁሟል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምልከታ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ 

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምልከታ አደረጉ 

(ሆሳዕና፣ሐምሌ 15/2018)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ 

መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በሆሳዕና ከተማ መሶብ 

የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመልክተዋል 

ርዕሰ መስተዳድሩ በተቋሙ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ሰራተኞችን 

የስራ እንቅስቃሴ በመመልከት አበረታተዋል። 

ህብረተሰቡ በተቋማቱ በስፋት መገልገል እንዲችል በትኩረት 

መስራት ተገቢ ስለመሆኑም ተናግረዋል። 

የሆሳዕና ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግት በ9 ተቋማት 30 

አገልግሎት እየሰጠ ነው። 

በክልሉ ሌሎች የመሶብ አገልግሎቶች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት 

ከመጀመራቸው በፊት ይህ ማዕከል ወደ ስራ በመግባት ረገድ ቀዳሚ ነው።

Read more
ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በጤና ተቋማት እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በጤና ተቋማት እየተሰጠ

ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል የክልሉ መንግስት በትኩረት

እየሰራ ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 15/2018፦ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕር ሄንሲቭ

ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ጋር ምክክር አድርገዋል 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በጤና ተቋማት

እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ

ነው ብለዋል።

የምንሰራው የቤተሰብ ብልጽግናን በማረጋገጥ ድህነትን ለማሸነፍ ነው

ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል።


የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕር ሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ

ሆስፒታል በቅብብሎሽ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲበቃ ላደረጉ አካላት

ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል። 

የጤና ስራ አድጋሚና በህዝብ እርካታ ላይ የተመሰረተ ነው ያሉት ርዕሰ

መስተዳድሩ ለዚህም የጤና ባለሙያዎችን እና የአመራሩን ቁርጠኝነት

ይጠይቃል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል። 

በሆስፒታሉ በሚሰጠው አገልግሎት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ደረጃ በደረጃ

ለመፍታት ጥረት መደረግ እንዳለበት ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

የስልጠና እና የምርምር ስራዎች ለጤናው ዘርፍ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ

የላቀ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።

Read more
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) መልዕክት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው ( ዶ/ር ) መልዕክት 

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከወስዱ ተማሪዎች 97 ነጥብ 

4 በመቶ የሚሆኑት ፈተናውን ማለፍ ችለዋል። 


ይህ ውጤት የመማር _ማስተማሩን ሂደት በማጠናከር፣ 

የመማር _ማስተማር ስነ ዘዴውንና የፈተና አስተዳደር 

ስርዓቱን በማሻሻል ፣ እና የተማሪዎች በራስ የመተማመን 

ስነ ልቦና እንዲጎለብት በተሠራዉ ተከታታይ የትምህርት 

ጥራት ችግሮችን የመቀልበስና የተማሪዎችን ውጤት የማሻሻል 

ሥራ የመጣ ነው።


ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጀምሮ በየደረጃው የምትገኙ የትምህርት 

ሴክተሩ አመራሮች እና ባለሙያዎች ፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራን፣ 

ተማሪዎች፣ የተማሪዎች ወላጆች፣ የየደረጃዉ የትምህርት አመራር 

ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ሌሎችም አካላት፣ዉጤቱ እንዲመዘገብ 

ላደረጋችሁት አሰተዋጽኦ በራሴ እና በክልሉ መንግስት ስም ምስጋናዬን 

አቀርባለሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለትም እወዳለሁ።

የትምህርት ጥራትን እና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተጀመረዉ 

ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ ።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የቡታጅራ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ሂደት ምልከታ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የቡታጅራ ከተማ 

የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ሂደት ምልከታ አደረጉ 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 6/2018፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ 

መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በቡታጅራ ከተማ 

በ544 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለውን የፍሳሽ ቆሻሻ 

ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል 

የቡታጅራ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ የከተማውን

ሳኒቴሽን አገልግሎት የሚያሳድግ ስለመሆኑም ተመላክቷል። 

ፕሮጀክቱ ከ243 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ 

እንደሚያደርግም ተጠቁሟል።

Read more
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )የሆሳዕና ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ሂደት ምልከታ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )የሆሳዕና ከተማ 

የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ሂደት ምልከታ አደረጉ 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 6/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ሆሳዕና ከተማ 

ከ588 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለውን 

የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል 

የሆሳዕና ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ የከተማውን 

ሳኒቴሽን በእጥፍ እንደሚያሳድገው ተመላክቷል። 

ለ1ነጥብ 5 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት 

የሚሰጠው ይህ ፕሮጀክት በቀን 250 ሜትር ኪውብ ውሃ 

በማጣራት ለመስኖ አገልግሎት እንዲውል የላቀ አስተዋጽኦ 

ያበረክታል። 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የሆሳዕና ከተማ 

የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ ሚያዚያ 29/2017 የመሰረት 

ድንጋይ በማስቀመጥ ግንባታ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

Read more
ርዕሰመስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከተረጂነትወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርትበጽ/ቤታቸው እየገመገሙ ነው

ርዕሰመስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት 

ከተረጂነትወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም 

ሪፖርትበጽ/ቤታቸው እየገመገሙ ነው 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 6/2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻውጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ ባለፉት 2 ዓመታት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት

 ለመሸጋገርየተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት እየገመገሙ ነው።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ባለፉት 2 ዓመታት በሀገር አቀፍም 

ሆነ በክልልአቀፍ ደረጃ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገር የሚያስችል 

ፕሮግራምበመቅረጽ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰው፤ 

የክልሉ መንግስት ለተከታታይ ሁለት ዓመታት በምግብ እራስን ለመቻል ዘርፈ 

ብዙ ጥረትሲያደርግ መቆየቱን ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክቷል። 

ከሚቀርበው ሪፓርት መነሻነት ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮችን በመለየት ዝርዝር 

ውይይትእንደሚደረግ አመላክተዋል።

Read more
የክልሉመስተዳደር ምክርቤት በአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀትአመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያየ፤ የቀጣይ ጊዜ ትኩረቶችንምአመላከተ

የክልሉመስተዳደር ምክርቤት በአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የ2018 

በጀትአመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያየ፤ የቀጣይ ጊዜ 

ትኩረቶችንምአመላከተ

ሆሳዕና፣ ሐምሌ 4/2018 ፦ 42 ተኛ መደበኛ ,ስብሰባዉን ያካሄደው 

የማዕከላዊኢትዮጵያ ክልል መስተዳደር ምክርቤት በክልሉ አስፈፃሚ 

መስሪያቤቶች የ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

ላይ ውይይትአድርጓል፤ የቀጣይ ጊዜ ትኩረቶችም ተመላክተዋል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ የክልሉ መንግሥት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች 

የእቅድአፈጻጸም በሁሉም የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የሰላምና ፀጥታ እና 

የመልካምአስተዳደር ዘርፎች ውጤታማና አበረታች እንደነበር በሪፖርቱ 

ተመላክቷል።

የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዓመታዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ሁኔታን

በተመለከተ፣ዓመታዊ ጠቅላላ ምርት ወይም የኢኮኖሚ ዕድገት በ10.2 

በመቶዓመታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ ተመላክቷል።

ጠቅላላ የክልሉ ዓመታዊ ምርትን በየክፍላተ ኢኮኖሚው አስመልክቶ 

በግብርናው ዘርፍ 8.1 በመቶ እድገት ማስመዝገብ መቻሉ በሪፖርቱ 

ተመልክቷል።

በኢንዱስትሪው ዘርፍ 21.8 በመቶ እድገት ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን 

በአገልግሎት ዘርፍ 10.5 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉ 

በሪፖርቱ ተገልጿል።

በግብርናው ዘርፍ የታረሰ መሬት አድጓል፣ የሰብል ምርትና ምርታማነት አድጓል፣ 

የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ መጠን መጨመሩ እንዲሁም 

የአገልግሎትዘርፍ ዕድገትም መጨመሩ ተመላክቷል።

Read more