Skip to main content

                                                                      የተቋሙ ስልጣንና ተግባር

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በባህሪዉ ከሌሎች ሴክተሮች በተለየ አግባብ የሚታይ ከመሆኑ አንፃር በተሻሻለው የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 74 (1-5) ለጽ/ቤቱ የተሰጠዉ ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ በክልሉ ህገ- መንግስት ለመስተዳድር ምክር ቤቱና ለርዕሰ መስተዳድሩ በአንቀጽ 70 እና 72 የተሰጡ ስልጣንና ተግባራትን ከማስፈፀም አኳያ ርዕሰ መስተዳድሩን በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች የሚደግፉ፣ ዝርዝር ጥናት በማድረግ የዉሳኔ ሀሳብ የሚያቀርቡ እና የሚያማክሩ እንዲሁም መስተዳድር ምክር ቤቱን የሚደግፉ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር እንደ ክልል መንግስት መሪነቱ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በተሳለጠ መንገድ ለማከናወን የሚያስችል አቅም ሊኖረዉ ስለሚገባ ለርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በህገ-መንግስቱ ከተሰጠዉ ስልጣንና ተግባር በተጨማሪ ለመስተዳድር ምክር ቤቱና ለርዕሰ መስተዳድሩ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራትን እየተከናወኑ ያሉ ተጨባጭ ስራዎችን መሰረት አድርገን ወስደናል፡፡