Skip to main content

በክልሉ በአንድ ጀንበር ከ10 ሚሊየን በላይ ችግኞች የመትከል ዘመቻ 

ተጠናክሮ ቀጥሏል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ሆሳዕና፣ሐምሌ 27/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር 

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በቀቤና ልዩ ወረዳ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን 

የችግኝ የተከላ መርሐ-ግብር ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

እንደገለጹት በሀገር አቀፍ ደረጃ 800ሚሊየን ችግኞች በአንድ ጀንበር 

ይተከላል ብለዋል። 

በክልሉ ከ10 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል ወደ ተግባር መገባቱን ርዕሰ 

መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

መላው የክልሉ ህዝብ በዛሬው እለት በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ እያካሄደ 

መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

በሀገር አቀፍ ደረጃ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ተቀምጦለት በክቡር ጠቅላይ 

ሚኒስትሩ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት ባለፉት ሰባት አመታት የአረንጓዴ አሻራ 

ፕሮግራም ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን አብራርተዋል። 

በአለም አቀፍ ደረጃ ኢተገማች የአየር ንብረት ለውጥ እየተከሰተ ስለመሆኑ 

የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ሊያጋጥሙን የነበሩ አደጋዎችን እየተከላከልን 

ነው ብለዋል። 

የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ህብረትን፣መደጋገፍን እና ሌሎች መልካም 

እሴቶቻችንን የሚያንጸባርቅ መሆኑን ጠቅሰዋል። 

አረንጓዴ አሻራ የጋራ ትርከክት መገንቢያ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 

በዚህም ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ያስተሳሰረ ነው ብለዋል። 

በክልሉ በእምነት ተቋማት፣በትምህርት ቤቶች፣በመንገድ አካፋዮች፣

በመዝናኛ ስፍራዎች እና በሌሎችም ተቋማት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም 

እየተካሄደ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

የሚተከሉት ችግኞች ለምግብነት፣ለኢንዱስትሪ ግብአት እና ለስነ ውበት 

አገልግሎት ጠቀሜታ እንዳላቸውም አብራርተዋል።

Image