admin11
Mon, 08/10/2026 - 09:57
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር
5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ።
ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ
ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ
መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው።
ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ቆይታው የክልሉን መንግሥት አስፈፃሚ
መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2019
በጀት ዓመት የእቅድ እቅጣጫዎች ላይ ይመክራል።
በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በኦዲት ቢሮ እና በምክር ቤት ጽ/ቤት
ያሳለፍነው በጀት አመት አፈጸምና በያዝነው በጀት አመት ጠቋሚ
እቅዶች ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል።
በጉባኤው የክልሉ የ2019 አጠቃላይ በጀት እንደሚታወጅ ይጠበቃል።
Image