በበጀት አመቱ ከ619ሺ በላይ ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ
ማድረግ ተችሏል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች
ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ
ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
እንደገለጹት በክልሉ በመንግስት፣በረጂ እና በአጋር አካላት ድጋፍ በገጠር እና
በከተሞች 207 የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ተችሏል።
ይህን ተከትሎም በበጀት ዓመቱ ከ619ሺ በላይ ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ
ተጠቃሚ ማድረግ ስለመቻሉም አመላክተዋል።
የመስኖ አውታር ግንባታን በሚመለከት 610 ሄ/ር የሚያለሙና 2ሺ 300 አባዎራና
እማዎራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የ5 ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ አገልግሎት
መስጠት መጀመራቸውን ጠቁመዋል።
በበጀት ዓመቱ ለ792 የማዕድን ማምረቻ ይዞታዎች ላይ ለባህላዊ እና ለአነስተኛ ደረጃ
ኮንስትራክሽን የማምረት የስራ ፈቃድ መሰጠቱን ተናግረዋል።
በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ስርጭት፣
አዳዲስ የቤተሰብ ባዮ ጋዝ ግንባታ፣የሶላር ማሾዎች ስርጭት እና መሰል ተዛማጅ
ስራዎች ተግባራዊ መደረጉን አብራርተዋል።