Skip to main content

መላው ህዝብ እና አመራር የጽዱ ኢትዮጵያን ንቅናቄ እውን 

ለማድረግ በሚካሄደው ጥረት ላይ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ 

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ጥሪ አቀረቡ 

ሆሳዕና ፣ነሐሴ 11/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 

"ጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ"በሚል መሪ ሀሳብ 3ኛ ዙር 

የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) 

በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ክልሉ ከተመሰረተ 

ሶስት ዓመታት አስቆጥሯል ብለዋል።በነዚህ የሶስት አመታት ጉዞ 

አዳዲስ ስኬቶችን ማስመዝገብ ስለመቻሉም ርዕሰ መስተዳድሩ 

በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል። 

ከነባሩ ክልል የተላለፈ እዳ ለመክፈል የተደረገው ርብርብ ውጤታማ ነው 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ግንባታቸው ተቋርጦ የነበሩ የመንገድ፣የንጹህ 

መጠጥ ውሃ፣የመስኖ፣የትምህርት እና የጤና ፕሮጀክቶች በጠንካራ 

ድጋፍና ክትትል ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን አብራርተዋል።

ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ ተቋማት ከ320 በላይ መለስተኛ እና መካከለኛ 

የልማት ፕሮጀክቶች በስራ ላይ መገኘታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

እነዚህ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ስራ ሲገቡ የክልሉን ህዝብ ተሳትፎ እና 

ተጠቃሚነት ያሳድጋሉ ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። 

በክልሉ የህዝብ አንድነት እና ተቀራርቦ የመስራት አቅም ለማሳደግ የጋራ 

ትርክትን መሰረት በማድረግ የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እና ለቀጣይ 

ስራ መሰረት የጣሉ ስለመሆናቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። 

ክልሉን 24 ሰዓታት ለስራ ምቹ እንዲሆን መደረጉን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ 

በተወሰኑ አካባቢዎች ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት ተከታታይ የሰላምና ጸጥታ 

ስራ ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል። 

በክልሉ የ2018 በጀት ዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት 10 ነጥብ 2 ማድረስ መቻሉን 

የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በግብርና 8ነጥብ 1፣ በኢንዱስትሪ 21ነጥብ 8 እንዲሁም 

በአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 10 ነጥብ 5 ማድረስ መቻሉን ጠቅሰዋል። 

በከተማ እና በገጠር ነዋሪውን ህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማሳደግ 

እየተካሄደ ያለው ጥረት በሁሉም መስኮች ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል። 

ጽዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለው ንቅናቄ 

የብልጽግናችን አካል ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል። 

የአካባቢ ብክለትን መከላከል ጤንነትን፣ምርታማነትን፣የመስራት አቅምን 

ያጎለብታል ብለዋል። 

መላው ህዝብ እና አመራር በዚህ ንቅናቄ ላይ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ 

እንዲወጣም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Image