Skip to main content

ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጋራ ትብብር እና ጥረት ያሻል:- ርዕሰ 

መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 

ሆሳዕና፣ነሐሴ 25/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
"ዘላቂ ሰላማችን ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"በሚል መሪ ሀሳብ 

በሆሳዕና ከተማ የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ነው 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ ጸጥታ 

ምክር ቤት ሰብሳቢ እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉባኤው እንደገለጹት 

የሰላም ዋጋ የሚታወቀው ሰላም ሲጎድል ብቻ ነው ብለዋል። 

ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጋራ ትብብር ያሻል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 

የበርካታ ተዋናዮችን ተሳትፎም ይጠይቃል ሲሉም ጠቁመዋል። 

ማህበረሰቡ ቤቱን አካባቢውን፣ጎረቤቱን መጠበቅ ይኖርበታል ያሉት 

ርዕሰ መስተዳድሩ የዚህ ድምር ውጤት በዘላቂ ሰላም ላይ የጎላ ሚና 

እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላከክተዋል። 

የጸጥታ ኃይሉ የማህበረሰቡን አቅም የማስተባበር፣የማቀናጀት ቀዬ፣

መንደር፣ ቀበሌዎች እና ወረዳዎች በሰላም ውለው እንዲያድሩ መትጋት 

ይኖርበታል ብለዋል። 

አንዳንድ ሀገሮች ተፈጥሮ በሚያደርስባቸው የሰላም ችግሮች ተጎጂ ሲሆኑ 

ተመልክተናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በኛ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ በሰው ሰራሽ 

የሰላም መደፍረስ ምክንያት የሚያጋጥመንን ችግር ለመፍታት የተቀናጀ 

ጥረት ይጠይቃል ሲሉም አስረድተዋል። 

ሚዲያዎች በሰላም ስራ ላይ የሚኖራቸው አበርክቶ ከፍተኛ ስለመሆኑም 

ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

አሁን ባለዉ ነባራዊ ሁኔታ በእያንዳንዱ ሰው የእጅ መዳፍ ስር ሚዲያ አለ 

ያያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከሁሉም በላይ ትኩረቱ በዘላቂ ሰላም ላይ ሊሆን 

እንደሚገባም ጠቅሰዋል። 

ለቤተሰብ ብልጽግና መረጋገጥ ሰላም የሚኖረው ድርሻ መሰረታዊ ነው 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የሁሉንም አካላት ቁርጠኝነት 

እንደሚጠይቅም አብራርተዋል። 

በየአካባቢው ለሰላም መደፍረስ መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ጉባኤተኛው 

በስፋት ሊመክርባቸው ይገባል ብለዋል። 

በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች በዘላቂ ሰላም ላይ ሊሰሩ እንደሚገባም 

ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። 

ክልሉ ከተመሰረተ ወዲህ የማምሸት ምጣኔ እየጨመረ መጥቷል ሲሉም 

ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። 

ህግ በማስከበር ስራ ላይ ምክር ቤቱ በዝርዝር መወያየት ይኖርበታል 

ሲሉም አብራርተዋል። 

የመንግስት ዋነኛ ሚና ህግ ማስከበር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ህግ 

እንዲከበር የሚፈልግ የማህበረሰብ ክፍል ሲኖር በሌላ በኩል ደግሞ ህግ 

እንዲከበር ፍላጎት የሌለው አካል መኖሩን ጠቁመዋል። 

ይህንን በማስታረቅ የህዝቡን ሰላም ማረጋገጥ አብይ አጀንዳ ሊሆን 

እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። 

ሰላም የሚጀምረው ከቤት፣ከጎረቤት፣ከአካባቢ መነሻነት ስለመሆኑም ጠቅሰዋል። 

በሀገሪቱ ወደ 4ሺ የሚጠጉ የኢትዮጵያ ልጆች በ8 ዋና ዋና አጀንዳዎች 400 

ንኡሳን አጀንዳዎች ላይ በመምከር 99በመቶ ምክረ ሀሳብ ማቅረባቸውን 

በአብነት ጠቅሰዋል። 

ይህን ምክረ ሀሳብ በመንቀፍ የሚዲያ ዘመቻ የሚያካሄዱ አካላት እንደነበሩም 

ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቁመዋል። 

ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የሚያጋጥሟትን ተግዳሮቶች በጽናት እና በድል አድራጊነት 

እየተሻገረች ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል

Image