በትምህርት ዘርፉ ውጤት ለማስመዝገብ የላቀ ድጋፍ እና ትብብር ይፈልጋል:-
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ሆሳዕና፣ነሐሴ 29/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 3ኛው የትምህርት
ሴክተር ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉባኤው
እንደገለጹት የትምህርት ስራ የላቀ ትብብር ይፈልጋል ብለዋል።
የትምህርት ስራ ተዋናዩ እና ባለድርሻ አካላት በርካታ ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ
በዘርፉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ልዩ ትኩረት ያሻል በማለት ገልጸዋል።
በማደግ ላይ ያሉ እና ያደጉ ሀገሮች ሀገራቸውን የለወጡት በትምህርት ነው ብለዋል።
በትምህርት ላይ ያላቸው አቋም ጠንካራ ስለነበረ ትምህርትን ተጠቅመው ሀገራቸውን
ገንብተዋል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
ፊላንድ፣ኖርዌይ፣ሲውዲን እና ሌሎች ሀገራት በትምህርት ላይ መስራት የጀመሩት
ከዛሬ 50 ዓመታት ገደማ እንደነበር ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል።
እንደ ቻይና የመሳሰሉት ሀገሮች የትምህርት ስርዓታቸውን ገምግመው መስራት
የጀመሩት የዛሬ 40 ዓመታት አካባቢ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
እነዚህ ሀገራት በትምህርት ላይ በሰሩት መጠን ሀገራቸውን መለወጥ መቻላቸውን
ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
ትምህርት የህዝብንም የመንግስትንም ትኩረት እንደሚያሻ ርዕሰ መስተዳድሩ
በንግግራቸው አብራርተዋል።
የአንድን ሀገር ስርዓት ለማቃናትም ሆነ ለማፍረስ ትምህርት ከፍተኛ ሚና እንዳለው
ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ትምህርት ከተጠቀምንበት ሀገራትን ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ በቀላሉ እንዲሸጋገሩ
ያስችላል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርትታሪክ የ110 ዓመታት እድሜ እንዳለው ርዕሰ መስተዳድሩ
ጠቁመዋል።
በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ችግሮች መንስኤ የትምህርት ውጤት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ
አለመከባበር እና የግብረ ገብነት ችግር ከዚህ ይመነጫል ሲሉም ጠቅሰዋል።