Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 47ኛ መደበኛ 

ስብሰባዉን አካሄደ

ሆሳዕና፣መስከረም 27/2019የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር

ምክር ቤት 47ኛ መደበኛ ስብሰባዉ በክልሉ በመቶ ቀናት እቅድ ላይ 

መክሯል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)

በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የክልሉን ጸጋዎች መሰረት በማድረግ በላቀ 

ቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል። 

አመራሩ ሁሉንም ስራዎች አቀናጅቶ በመስራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ 

ላይ ማተኮር አለበት ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። 

የክልሉን እና የህዝቡን አንድነት በመጠበቅ፣በማጽናት እና በማላቅ ማሻገር 

ተገቢ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

አጠቃላይ የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ የሚገልጽ የሁኔታ ትንተና ማካሄድ ተገቢ 

ስለመሆኑ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ መቶ ቀናት ትኩረት 

በሚደረግባቸው አበይት ጉዳዮች ላይ የጋራ ተግባቦት መፍጠር የሚያስችል 

መድረክ መሆኑን አመላክተዋል። 

በሁሉም ዘርፍ ውጤት ለማስመዝገብ አቅምን እና ትኩረትን በማሰባሰብ 

በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባም ርዕሰ መሰስተዳድሩ አጽንኦት 

ሰጥተዋል። 

በሚቀጥሉት መቶ ቀናት ተግባራዊ የሚደረጉ ስራዎችን ለማሳካት ቅንጅታዊ 

አሰራር መፍጠር እንደሚገባም አብራርተዋል። 

ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስርዓት በማጠናከር ተጨባጭ ውጤት እንዲመዘገብ 

መስራት ይገባል ሲሉም ጠቅሰዋል። 

አመራሩ መላውን ሰራተኛ በማስተባበር ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር ይገባል 

ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የሁሉንም አካላት የላቀ ጥረት 

እንደሚጠይቅም ተናግረዋል። 

የስራ ባህል ለውጥ ማድረግ ለተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ወሳኝ ስለመሆኑም 

አብራርተዋል።

Image