Skip to main content

የመደመርመንግስት ዋና ዓላማ እንደ ሀገር የኢትዮጵያን ስልጣኔ 

መገንባትነው :-ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) 

ሆሳዕና ፣ ጥቅምት 2/2019 ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአመራር 

መድረክበሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) 

እንደገለጹትየመደመር መንግስት ምስረታ ታላቅ ህዝብ፣ታላቅ ሀገር 

ታላቅራዕይ የሚል መሪ ቃል መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል። 

መሪቃሉጥልቅ መልዕክትን ያዘለ ስለመሆኑ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ 

የመደመርመንግስት እሳቤዎችን መሰረት በማድረግ ለስራችን ስኬታማነት 

መጠቀምይገባል ሲሉም አብራርተዋል። 

የመደመር መንግስት ዋና ዓላማ ስራዎችን በተለመደው መንገድ ተግባራዊ 

ማድረግሳይሆን አዲስ አሰራር በመፍጠር የኢትዮጵያን ስልጣኔ መገንባት 

ስለመሆኑምአመላክተዋል። 

ያለንን አቅም በማሰባሰብ በስፋት አምርተን ኢኮኖሚያችንን አሳድገን ፣

የህዝባችንንተጠቃሚነት አረጋግጠን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማሳካት 

ይገባልብለዋል። 

ስልጣኔ ከሁለንተናዊ ብልጽግና የሚሻገር ጉዳይ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ 

አመላክተዋል።

እየመሰረትነው ያለነው መንግስት የተለመደው አይነት አመራር አለመሆኑን 

መገንዘብተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። 

በክልሉ ተግባራዊ በሚደረጉ ስራዎች፣በሚታቀዱ እቅዶች፣ትልቁ አቅማችን 

የመጀመሪያውእናየማይተካው ሚና የአመራሩ ነው ብለዋል። 

የዚህ አመራር አንድነት እና ጥንካሬ ካልተረጋገጠ ለአንድ አላማ መስራት 

ካልቻለውጤት ማስመዝገብ አዳጋች ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

Image