admin
ቲዩ, 01/28/2025 - 16:18
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የግብርና ኤግዚቢሽን እና ባዛር መርቀው ከፈቱ
ሆሳዕና፣ጥር 14፣2017፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ ግብርና ቢሮ የተዘጋጀውን የግብርና ኤግዚቢሽን እና ባዛር በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ መርቀው ከፍተዋል።
በኤግዚቢሽን እና ባዛሩ የክልሉን የመልማት አቅም እና የግብርናውን ዘርፍ ውጤታማነት መለየት እንደሚያስችልም ተመላክቷል።
በክልሉ ከዚህ ቀደም ያልተለመዱ የግብርና ምርቶችን በአይነት በብዛት እና በጥራት የማምረት ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።
በኤግዚቢሽን እና ባዛሩ የቡና፣የቅመማ ቅመም፣የቅባት እህሎች፣ልዩ ልዩ ሰብሎች እና ሌሎች የግብርና ምርቶች ለእይታ በቅተዋል።
#ከክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን
Image
