ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ
የልማት ስራዎች ምልከታ እያደረጉ ነው
(ሆሳዕና ፣ጥቅምት 8/2019)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ
መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ የልማት
ስራዎች ምልከታ አድርገዋል
በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ ልኡክ የወልቂጤ አጠቃላይ ሆስፒታል
አሁናዊ የግንባታ ሂደት ምልከታ አካሂዷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማው ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን
የክልል ተቋማት ቢሮ ህንጻ ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በጉራጌ ዞን የኢንቬስትመንት ፕሮጀክቶች የመስክ ስራ
ምልከታቸው አድርገዋል።
በዞኑ 396 የኢንቬስትመንት ፕሮጀክቶች መኖራቸው የተመላከተ ሲሆን
ከ25ሺ ሄ/ር በላይመሬት መተላለፉም ተጠቁሟል። በዚህም ከ32 ሺ በላይ
ዜጎችቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ የቲናው ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር እና የቪታሳሉቲ
ማኑፋክቸሪንግ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
የቲናው ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር ከ50 ሚሊየን በላይ የአበባ ዘንግ በማምረት
ለውጭገበያ እያቀረበ መሆኑም ተመላክቷል።
በአመት ከ11 ሚሊየን በላይ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ የሚገኝ ፕሮጀክት
መሆኑም ተጠቁሟል።
በጥቂት አመታት ውስጥ እስከ 25 ሚሊየን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ለማግኘት
መታቀዱንም በመስክ ምልከታው ገለጻ ተደርጓል።