Skip to main content

የሀይማኖትአባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በክልሉ ሁለንተናዊ 

ሰላምናጸጥታ ላይ የጎላ አበርክቶ አላቸው:-ርዕሰ መስተዳድር 

የትምጌታአስራት (ዶ/ር) 

ሆሳዕና ፣ጥቅምት 13/2019፦"በመደመር መንግስት ህብረተሰብ 

አቀፍየምክክር መድረክ በዱራሜ ከተማ ተካሂዷል 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት 

(ዶ/ር)በምክክር መድረኩ ማጠቃለያ እንደገለጹት የመደመር 

መንግስትጸጋዎችን አልምቶ የህዝብ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል 

ብለዋል።

የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በክልሉ ሁለንተናዊ 

ሰላምናጸጥታ ላይ የጎላ አበርክቶ እንዳላቸው ጠቅሰዋል። 

ህግማስከበር እንዲሁም የጸጥታ መዋቅር አቅም በመገንባት ዘላቂ 

ሰላምንማረጋገጥ ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል። 

ህዝቡ የሚያነሳቸውን የሰላም፣የልማት እና የመልካም አስተዳደር 

ጉዳዮችበማዳመጥ የክልሉ መንግስት ምላሽ ለመስጠት ያላቸውን 

ቁርጠኝነትአረጋግጠዋል። 

የመደመር መንግስት አብይ ጉዳይ ችግሮችን መፍታት እና የህዝቡን 

ኑሮ ማሻሻልመሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። 

የመንገድን ችግር በሚገባ እረዳለሁ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዘርፉ 

እየተነሳያለውን ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሰራም ርዕሰ 

መስተዳድሩጠቁመዋል። 

በመብራት፣በንጹህ መጠጥ ውሃ፣በጤና፣በትምህርት እና በሌሎችም 

መሰረታዊየልማት ጥያቄዎች ላይ የሚነሱ ጉዳዮችን ለመፍታት የክልሉ 

መንግስትያለውን ዝግጁነት ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። 

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው የመጨረሻው ግባችን የኢትዮጵያን 

የመደመርስልጣኔ መገንባት ነው ብለዋል።

የባህር በር ጉዳይ የሉአላዊነት እና የህልውና ጉዳይ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ 

አብራርተዋል።

የመደመር መንግስት በስፋት የሚያመርት፣ስራ ፈጣሪ፣ከህዝብ፣መንግስታዊ 

ካልሆኑተቋማት እንዲሁም ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር የሚሰራ ነው ሲሉም 

ርዕሰመስተዳድሩ ጠቁመዋል።

Image