admin11
Mon, 10/26/2026 - 09:49
ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በከምባታ ዞን ልዩ ልዩ
የልማት ፕሮጀክቶች ተመለከቱ
ሆሳዕና ፣ጥቅምት 13/2019፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ
መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በከምባታ ዞን ልዩ ልዩ የልማት
ፕሮጀክቶችን ተመልክተዋል።
በዞኑ ከህዝባዊ የምክክር መድረክ በተጓዳኝ በመንግስት እና በግል
ባለሀብቶች ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ስራዎችን ተመልክተዋል።
በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልኡካን ቡድን የዱራሜ- ዳንቦያ-
አንጋጫ- አመቾ ዋቶ- ሀላባ የኮንክሪት አስፖልት መንገድ ግንባታ
ስራ ፕሮጀክት አፈጻጸም ተመልክቷል።
በዞኑ በሀምበሪቾ ዳግም 777 የሚሰሩ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች፣የዱራሜ
ከተማ የኮሪደር ልማት፣ማቴዎስ ኤርሱሞ ፒፒ ከረጢት ማምረቻ
ፋብሪካ እንዲሁም በወጣት አብነት ዲላሞ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ
የልማት ስራዎች ምልከታ አድርገዋል።
Image