የክልሉ መንግስት ከህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ላይ
ያተኩራል :-ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)
ሆሳዕና ፣ጥቅምት 14/2019፦"በመደመር መንግስት ህብረተሰብ አቀፍ
የምክክርመድረክ በሙዱላ ከተማ ተካሂዷል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)
በምክክር መድረኩ ማጠቃለያ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ከህዝብ
ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ላይ ያተኩራል ብለዋል።
የመደመር መንግስት በመደመር እሳቤ የሚመራ የመደመር ስትራቴጂን
ያነገበ እና ለህዝብ ጥቅም የሚሰራ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
ለምመሬት ታታሪ ህዝብ፣ውሃ፣ልዩ ልዩ ማዕድን ያለን ህዝቦች መሆኑን
ተከትሎ ድህነትን ለማሸነፍ መስራት ተገቢ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
በእውነት እና በፍትህ የምንተጋበት ጊዜ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ
በልማት እና በመልካም አስተዳደር ላይ ህዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች
በተገቢው መንገድ ምላሽ መስጠት ልዩ ትኩረት እንደሚያሻም ጠቅሰዋል።
የምንሰጠው ውሳኔ የህዝቡን ኑሮ ማሻሻል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይሆናል
ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ከምንም በላይ ለህዝብ ጥቅም መስራት ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ
በየደረጃው የሚነሱ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የአመራሩን ቁርጠኝነት
ይጠይቃል ሲሉም ጠቅሰዋል።
በመንገድ፣በንጹህ መጠጥ ውሃ፣በጤና ፣በትምህርት እና በሌሎችም የመሰረተ
ልማት ተደራሽነት ላይ በልዩ ትኩረት እንሰራለን ሲሉም ጠቁመዋል።
እንደ ሀገር የመደመር ስትራቴጂ መቀረጹ ዘመን ተሻጋሪ የብልጽግና መሰረት
መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ሊለማ የሚችል መሬት፣የሰለጠነ የሰው ሀይል ትጉህ አርሶ አደር እያለን ለድህነት
ተጋላጭ ሆነናል ብለዋል።
ይህንን የተቃርኖ ጉዞ ማቃናት እና የህዝቡን ህይወት በዘላቂነት ማሻሻል
እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የተበታተነውን አቅም በማሰባሰብ የህዝቡን ኑሮ ለመቀየር ስራ ላይ ማዋል
እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በቅንነት፣በታማኝነት እና በእውነት ህዝብን ማገልገል እንደሚገባም ርዕሰ
መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።