Skip to main content

ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በሀላባ ዞን ልዩ ልዩ 

የልማት ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ 

ሆሳዕና ፣ጥቅምት 15/2019፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ 

መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በሀላባ ዞን ልዩ ልዩ የልማት 

ፕሮጀክቶች እየተመለከቱ ነው

ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ በነበራቸው ቆይታ በህዝብ ተሳትፎ የተገነባውን 

የሀላባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተመልክተዋል። 

በከተማው በግንባታ ላይ የሚገኘውን የክልል ተቋማት ህንጻ አፈጻጸም 

ምልከታ አድርገዋል። 

የሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ሞዴል የአትክልትና ፍራፍሬ ኩታ 

ገጠም እርሻ በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልኡክ ተመልክቷል። 

በሆስፒታሉ ከሚሰጠው የጤና አገልግሎት በተጓዳኝ በሆስፒታሉ የተጀመረው 

የፍራፍሬ መንደር ለበርካታ አርሶ አደሮች በተሞክሮነት ተነስቷል። 

በሀላባ ዞን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ(ዶ/ር) የተጀመረውን ኢኒሼቲቭ 

ቀጣይነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው። 

ይህን ተከትሎም በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ ልኡክ በዞኑ ዌራ ወረዳ የገጠር 

ኮሪደር ግንባታ ተመልክቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በዚሁ 

ጊዜ እንደገለጹት በከተማ እና በገጠር የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በጥራት እና 

በፍጥነት መጠናቀቅ አለባቸው ብለዋል። 

በዞኑ እየተገነባ የሚገኘው የገጠር ኮሪደር ልማት በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት 

መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል።

 

Image