የመደመርመንግስት የጤናው ዘርፍ ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ዘርፈ
ብዙስራዎችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል:- ርዕሰ መስተዳድር
የትምጌታአስራት (ዶ/ር)
ሆሳዕና፣ጥቅምት 28/2019፦28ኛው የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ
በሆሳዕናከተማ እየተካሄደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)
በክልሉእየተካሄደ የሚገኘው ሀገር አቀፍ የጤና ጉባኤ የጤናውን ዘርፍ
ልማትወደፊት የሚያራምዱ፣በሳል ውይይቶች እና የልምድ ልውውጦች
የሚደረጉበትነውብለዋል።
በጉባኤው ለአዳዲስ ውጤቶች መንደርደሪያ የሚሆኑ አቅጣጫዎች
እንደሚቀመጡበትይጠበቃል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
ጉባኤው በመደመር መንግስት ምስረታ ማግስት እንደ አንድ ልብ መካሪ
እና እንደአንድ ቃል ተናጋሪ በአንድ ገጽ ላይ የምንገኝበት ነው ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ወቅቱን የዋጀ የጤና ስርዓት ለመገንባት
የጋራተግባቦት የምንፈጥርበት እና በዘርፉ ያለንን ዝግጁነታችንን
የምናረጋግጥበትነውሲሉም ጠቁመዋል።
ተለዋዋጭ እና ኢተገማች በሆነው አለም ዓቀፋዊ ሁኔታ ውስጥ በአሰራር፣
በአደረጃጀት፣በሰውሀይል የተጠናከረ የጤና ስርዓት ከመገንባት ባሻገር
ጠንካራየዘመነ ዲጂታል የጤና ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ ስለመሆኑም
ርዕሰመስተዳድሩ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን የሚሆነው አካላዊ እና አእምሯዊ
ጤንነቱየተጠበቀ ብቁና ንቁ ዜጋ ሲገነባ መሆኑን ጠቅሰዋል።
መንግስት የጤናው ዘርፍ ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን እና ሀብረተሰባዊ እርካታን
ለማረጋገጥበሚያስችል መልኩ እንዲጠናከር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ተግባራዊ
እያደረገይገኛል ብለዋል።
ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረውን የጤና ፖሊሲ በማዳበር በሽታን አስቀድሞ
ከመከላከልባሻገር አክሞ በማዳን ላይ እንዲያተኩር ተደርጎ ሁሉንም አይነት
በሽታዎችንመከላከል እና መቆጣጠር ላይ ትኩረት ተደርጓል ሲሉም ርዕሰ
መስተዳድሩአስረድተዋል።
በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት በጤናው ዘርፍ በርካታ ስራዎች ተግባራዊ
ተደርጓልያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች
ቁጥርከአንድ ወደ 3 ከፍ ማድረግ መቻሉን በአብነት ጠቅሰዋል።
በክልሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ቁጥር ከ19 ወደ 25 የጤና ጣቢያዎች
ቁጥርከ219 ወደ 244 ማደጉን ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል።
የኮምፕሬንሲፍ ጤና ኬላዎች ከስድስት ወደ 25 መድረሱን የተናገሩት ርዕሰ
መስተዳድሩሞዴል የማህበረሰብ መድሀኒት ቤቶች ከ5 ወደ 40 ማሳደግ
መቻሉንአብራርተዋል።
በክልሉ የጤና አገልግሎቶች ተደራሽነት እና ጥራት እየተሻሻለ መምጣቱን ርዕሰ
መስተዳድሩበአብነት ጠቅሰዋል።