የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን
ማድረግና የመድሃኒት አቅርቦትን ማሳለጥ የአመራሩ ቁልፍ ተግባር ሊሆን
ይገባል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አሥራት (ዶ/ር)
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀ
እንዲሆን ማድረግና የመድሃኒት አቅርቦትን ማሳለጥ የዘርፉ አመራር
ቁልፍ ተግባር ሊሆን ይገባል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ
መስተዳድር የትምጌታ አሥራት (ዶ/ር) ገልጸዋል ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የንቅናቄ
መድረክ ማጠቃለያ ላይ እንዳሉት ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ ያላውን
የጤና መድህን የአገልግሎት ጥራት በማሳደግና የመድሃኒት አቅርቦትን
በማሳደግ የህዝቡን የጤና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የአመራሩ ቁልፍ
ግብ መሆን አለበት።
የዜጎች፣የህዝብ ጉዳይ የአመራሩ ተቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት ሲሉም
ተናግረዋል ።
በተለይ ጤና የህዝብ የመብትና በህይወት የመኖር ጉዳይ ነው ያሉት ርዕሰ
መስተዳድሩ ይህን የህዝብ መብት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል ።
የአመራሩ ተልእኮ ለህዝብ ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ መስጠት እንደሆነም
ጠቁመዋል ።
በጤና መድህን የሚሰበሰብ ገንዘብን በተገቢው መንገድና በወቅቱ ማስገባትና
ኦዲትን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸው፤
ይህን በማያደርጉ አካላት ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም ርዕሰ መስተዳድሩ
አሳስበዋል ።
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎቶችንና ቁልፍ ተግባራትን ዲጅታይዝ
ማድረግ ይገባል ያሉት ዶ/ር የትምጌታ
በማህበረሰብ መድሃኒት ቤቶች መስፋፋት ፣በአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ላይ
ትኩረት ልዩ ትኩረት መደረግ አለበት ብለዋል።