Skip to main content
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር ) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የባንኩ የሆሳዕና ዲስትሪክት አመራሮች ጋር ተወያዩ ፤
ሆሳዕና ፣ ጥር 16 ፣ 2017፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር ) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንትና የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሀላፊ እና ከሆሳዕና ዲስትሪክት አመራሮች ጋር ባንኩ የክልሉን የልማት ሥራዎችን ይበልጥ መደገፍ በሚችልባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸዉ ምክክር አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንትና የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሀላፊ አቶ ሙሉነህ ለማ ፣ የባንኩ የሆሳዕና ዲስትርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ምስጋና ለጌታ ግርማ ፣ በሆሳዕና ዲስትሪክት የነጋዴ ደንበኞችና የከፍተኛ ደንበኞች ሀላፊ አቶ ጌታሁን ሽጉጤ በምከክር መድረኩ የተገኙ ሲሆን፣ የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪዎች ቡድንም በመድረኩ ተገኝቷል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ ( ዶ/ር ) አጠቃላይ የክልሉን ኢንቬስትመንት ልማት ዘርፎች ለማበረታታት ባንኩ የጀመረዉን ጥረት እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት፣ ለመኖሪያ ቤት ልማት፣ ምርትና ምርታማነትን ለሚያሻሽሉ እንደ ምርጥ ዘርና መሰል ግብዓቶችን ለማመቻቸት በሚያግዙ መስኮች ለተሠማሩ ባለሀብቶችና ህብረት ሥራ ማህበራትም ባንኩ ድጋፉን እንዲያጠናክር አሳስበዋል ።
ባንኩ እና ክልሉ በጋራ የሚሠሯቸዉን ጉዳዮች የተመለከተ ክልላዊ ጥናትም ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ርዕሰ መስተዳድሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።
የባንኩ አመራሮችም ተቀራርቦ በመሥራት የኢኮኖሚ ግንባታዉን ሂደት ለመደገፍና የደንበኞችን ፍላጎት ለሟሟላት በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል ።
Image
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር ) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የባንኩ የሆሳዕና ዲስትሪክት አመራሮች ጋር ተወያዩ ፤