በሌማት ትሩፈት ከቤተሰብ እና ከማህበረሰብ ተጠቃሚነት ባለፈ
ወደ ፋብሪካ መሸጋገር እንደሚቻል ተመልክተናል :-
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ሆሳዕና፣ግንቦት 17/2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሀዲያ ዞን የሊቻ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ
ዩኒየን የወተት ማምረቻ፣ማቀነባበሪያ እና የግብይት ማዕከል ስራ አስጀመሩ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ የወተት ማቀነባበሪያዎች ስራ መጀመር
የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያሳድጋል ብለዋል።
የሊቻ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ከዚህ ቀደም በዘርፉ
የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
አሁን በትንሽ አቅም የተጀመረው ጥረት የወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች
በማምረት በኢኮኖሚው ላይ የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።
ማቀነባበሪያው አርሶ አደሩን የፋብሪካ ባለቤት በማድረግ ኢኮኖሚያዊ
ተጠቃሚነቱን እንደሚያሳድግሞም ጠቁመዋል።
የወተት እና የወተት ተዋጽኦው በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ
እንዲሆን በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
የሌማት ትሩፈት ከቤተሰብ እና ከማህበረሰብ ተጠቃሚነት ባለፈ ወደ
ፋብሪካ መሸጋገር እንደሚቻል ተመልክተናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ
ምርቶቹን ወደ ሌሎቹ የሀገሪቱ ክልሎች ማስፋፋት ይገባል ብለዋል።
በሌማት ትሩፈት ከቤተሰብ እና ከማህበረሰብ ተጠቃሚነት ባለፈ
ወደ ፋብሪካ መሸጋገር እንደሚቻል ተመልክተናል :-
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)