Skip to main content

ዲጂታል  አገልግሎትን  ተደራሽ  በማድረግ  ዜጎች  ቀልጣፋ  አገልግሎት 

እንዲያገኙ  ይሰራል - እንዳሻው  ጣሰው  (ዶ/ር) 

ሆሳዕና ፣ ግንቦት 26፣ 2018 ዲጂታል አገልግሎትን በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች

ተደራሽ በማድረግ ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ይሰራል አሉ 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ከ260 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ 

የተገነባውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በዛሬው ዕለት መርቀው 

ሥራ አስጀምረዋል። 

በማዕከሉ 6 የተለያዩ ተቋማት 20 አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ጠቁመው፤ 

በቀጣይ ይበልጥ እየሰፋ ይሄዳል ብለዋል፡፡

ቴክኖሎጂውን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ ዜጎች የተቀላጠፈ 

አገልግሎት እንዲያገኙ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማዋ ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት 

መስጠት የሚችል የገበያ ማዕከልም መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

መንግስት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን

ለመፍታት ዲጂታል አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ላይ ነው ብለዋል።

ዛሬ በወራቤ ከተማ ተገንብቶ ወደ ስራ የገባው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 

የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ቋት በመስጠት የማህበረሰቡን እንግልት 

ያስቀራል ነው ያሉት።

መንግሥት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን እውን በማድረግ የማህበረሰቡን ችግር 

ለመፍታት በቅንጅት እየሰራ ይገኛል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ተደምጠዋል።

Image