Skip to main content

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ
በበሊሎ ወንጪሶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል

ክልል አቀፍ ፈተና አስጀመሩ

ሆሳዕና ፣ ሰኔ 11/2018፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ በበሊሎ ወንጪሶ ሁለተኛ ደረጃ

ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ተማሪዎች በራስ የመተማመን አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ

መክረዋል።

ተማሪዎች በክልል አቀፍ ፈተናው የላቀ ውጤት አንዲያስመዘግቡም ርዕሰ መስተዳድር

መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ 87ሺ 876 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መውሰድ ጀምረዋል።

ለዘንድሮው ክልል አቀፍ ፈተና ፈታኞች፣ሱፐርቫይዘሮች እና ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች

ተመድበው እየሰሩ መሆኑም ተመላክቷል።

Image