ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ(ዶ/ር ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተመሠረተበትን ሁለተኛ ዓመት አስመልክተዉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ የመልዕታቸዉም ሙሉ ይዘት የሚከተለዉ ነዉ፦
admin11
Wed, 08/20/2025 - 11:00
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ(ዶ/ር ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተመሠረተበትን ሁለተኛ ዓመት አስመልክተዉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ የመልዕታቸዉም ሙሉ ይዘት የሚከተለዉ ነዉ
ለመላዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች፣
ክልላችን ለተመሠረተበት ሁለተኛ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ!አደረሰን !
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተመሠረተበት ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓመተ ምህረት እነሆ ሁለት ዓመት ሆነዉ።
እነዚህ ሁለት የትግልና የስኬት ዓመታት ፦በሁሉም መስኮች ተጨባጭ ዉጤቶች የተመዘገቡባቸዉ ፣በየምዕራፉ ካገጠሙ ፈተናዎች ትምህርት የተወሰደባቸዉ፣ የሕዝቦች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ የመጣባቸዉ፣ ሠላማዊ ፣ ጠንካራና ምሳሌ ሊሆን የሚችል ክልል ለመፍጠር የሚያስችሉ ምቹ መደላድሎች እዉን የሆኑባቸዉ፣